1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ጥር 4 2001

ሊቨርፑል ነጥብ ተጋርቶ፣ ቸልሲ ነጥብ ጥሎ ካሉበት ብዙም ፈቅ ባላሉበት ሁኔታ፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ የነጥብ ዩነቱን እያጠበበው ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታዎቹን ካሸነፈ፤ ሊቨርፑልን በአንድ ነጥብ በልጦ መሪነቱን የመረከብ ዕድል አለው።

https://p.dw.com/p/GWjP
ተስፋ የተጣለበት ክርስቲያኖ ሮናልዶ
ተስፋ የተጣለበት ክርስቲያኖ ሮናልዶምስል picture-alliance/ dpa
ሞሪንሆ ቸልሲ ብቆይ የቀድሞ ቡድኔን ለድል አበቃው ነበር ሲሉ ተናገሩ፤ የስኮላሬን ብቃት ግን ሳያደንቁ አላለፉም። ዲዲየር ድሮግባና ሚካኤል ኤሲየን የአፍሪቃ ምርጥ ተጫዋቾች ሆነው በ CAF ለዕጩነት ቀርበዋል፤ ሁለት ግብፃውያንም አብረዋቸው ይገኛሉ። ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ FIFA መስፈርት የዓለም ምርጥ ተጫዋች ሆኖ እንደሚመረጥ ይጠበቃል። የእንግሊዝ ፣ የጣሊያንና የስፔን የሊግ ውድድሮች ውጤትና የደረጃ ሰንጠረዦችንም ይዘናል፤ አትሌቲክስ ነክ ዜናዎችም ይኖሩናል።