1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሥለ አካባቢ ጥበቃ የቡድን 20 ጉባዔ

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 1 2008

ሐንግሹ- ቻይና ዉስጥ የተደረገዉ የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ከዚሕ ቀደም ከተለመደዉ የኢኮኖሚና የገንዘብ ነክ ጉዳዮች ወጣ ብሎ ሥለተፈጥሮ ጥበቃ መነጋገሩ ብዙዎችን ሲያስገርም፤ ለተፈጥሮ ጥበቃ ተሟጋቾች ተስፋ ሰጥቷል።

https://p.dw.com/p/1Jwho
G20 Gipfel Vorbereitungen
ምስል picture-alliance/dpa/Xinhua/Y.Dongxun

ባለፈዉ ዕሁድ ተጀምሮ ትናንት በተጠናቀቀዉ ጉባዔ ላይ በተለይ ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና የዓየር ንብረት ለዉጥን ለመቀነስ ከዚሕ ቀደም ፓሪስ-ፈረንሳይ ላይ የተደረሰበትን ሥምምነት ማፅደቃቸዉ እንደ ጥሩ ዉጤት ነዉ የታየዉ። ይሁንና የተፈጥሮ ሐብትን ለመጠበቅ አሁንም ብዙ ጥረት እንደሚጠይቅ ባለሙያዎች ይናገራሉ።የዛሬዉ ጤና እና አካባቢ የቡድን 20 ጉባዔንና ዉጤቱን ይቃኛል። የዶይቼ ቬለዋ ሃና ፉክስ የዘገበችዉን የበርሊኑ ወኪላችን እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።


ሃና ፉክስ / ይልማ ሐይለ ሚካኤል


ነጋሽ መሐመድ