1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስኬት መንገድ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 2001

አፍሪቃ ውስጥ ከአስተማሪነት እስከ መኪና መካኒክነት! ከግብርና እስከ ጋዜጠኝነት፦ ብዙ ጥሩ ጥሩ የሥራ እድሎች አሉ። ይሁን እንጂ ብዙ ሰዎች የተውሰኑ የስራ መስኮችን ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ። በማዳመጥ መማር የተሰኘውን ዝግጅት አድማጮች የሚ ያልሙትን ስራ ማግኘት ስለሚ ችሉበት ሁኔታ ተግባራዊ የሆነ ምክር ይሰጣል።

https://p.dw.com/p/Fexm
ምስል laif

የስኬት መንገድ

አፍሪቃ ውስጥ ከአስተማሪነት እስከ መኪና መካኒክነት! ከግብርና እስከ ጋዜጠኝነት፦ ብዙ ጥሩ ጥሩ የሥራ እድሎች አሉ። ይሁን እንጂ ብዙ ሰዎች የተውሰኑ የስራ መስኮችን ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ። በማዳመጥ መማር የተሰኘውን ዝግጅት አድማጮች የሚ ያልሙትን ስራ ማግኘት ስለሚ ችሉበት ሁኔታ ተግባራዊ የሆነ ምክር ይሰጣል።

ለኔ የተሻለው ራ የትኛው ነው? አንዳንድ ጊዜ ለዚህ ለመነሻው እርምጃ መልስ መስጠት ቀላል ነገር አይደለም። ዘጋቢዎቻችን የተለያዩ ሙያተኞችን በማነጋገር ለኔ የተሻለው ራ የትኛው ነው? ለሚ ለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ይሞክራሉ። ለምሳሌ እንዴት ሙዚቀኛ መሆን እንደሚቻል! ለአንድ የሆቴል ራ አስኪያጅ ሕይወት ምን እንደምትመስል እና የመሳሰሉትን ለማሳየት ይሞክራሉ። አስተማሪ ወይም ደግሞ የኮምፒዩተር ባለሙያ ለመሆን ምን እንደሚ ያስፈልግም ይጠቁማሉ።

አስፈላጊው ስንቅ

ተከታታይ በሆኑ ዘገባዎች አድማጮች አንድ ጥሩ ራ ለማግኘት ስለሚያስችላቸው ትምህርት በዝርዝር ይቀርብላቸዋል። በማዳመጥ መማር አድማጮች ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ ለመማር የሚያስፈልጋቸው ገንዘብ፤ እዛ ከገቡ ደግሞ አዲሱን ሕይወት እንዴት መላመድ እንደሚችሉ፤ ሲያጡናቅቁም ራ ለማግኘት እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው ያስተምራቸዋል።

እየተዝናናን እንማር

በገሃዱ ዓለም ከሚኖሩ ሰዎችጋ ከሚደረገው ጨዋታ በተጨማሪ በማዳመጥ መማር ሌሎች የመዝናኛ ዝግጅቶችን ያቀርባል። የሬድዮዉ ጭውውት አንዲት ወጣት ሴት ከገጠር ወደ ከተማ በግብርና የዲግሪ መርኀ ግብር ለመማር ሄዳ የከተማውን ሕይወት ለመላመድ ያጋጠማትን ውጣውረድ፤ እንዲሁም የቃኘችውን የግቢ ሕይወት አድመጮች እንዲከታተሉት ይደረጋል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ይቀርባል። ቋንቋዎቹም አማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ናቸው። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎን www.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል::