1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሥነ ቴክኒክና የኢንዱስትሪው አብዮት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 2004

በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ፍጻሜ ፣ እ ጎ አ ሚያዝያ 6, 1896 ዓ ም ፤ የአዲሱ ዘመን የኦሊምፒክ እስፖርት ውድድር ፤ ጥንት በተጀመረባት ሀገር ግሪክ መዲና ፤ አቲና እንደገና እንዲያንሠራራ ከተደረገ ወዲህ፣ በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም

https://p.dw.com/p/15hu0
ARCHIV - Hinter Strommasten steigt Rauch vom RWE-Braunkohlekraftwerk Niederaußem bei Bergheim in die Höhe. (Archivfoto vom 04.04.2007). Die Kraftwerkstechnologie ist in der Klima-Debatte schon lange ein Zankapfel. Umweltschützer werfen Industrie und Politik vor, noch immer zu stark auf vergleichsweise schmutzige und ineffiziente Kohlekraftwerke zu setzen und zu wenig für die Erschließung erneuerbarer Energien zu tun. Foto: Oliver Berg dpa (zu dpa-KORR.: "Zankapfel Kraftwerk. Kohle-Neubauprojekte schüren Sorgen ums Klima" vom 12.06.2007) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

ጦርነት ከመቋረጡ በስተቀር፤ በ የ 4 ዓመት አንድ ጊዜ ሲካሄድ መቆየቱ የታወቀ ነው።የአዲሱ ዘመን የኦሊምፒክ እስፖርት ውድድር  ለ 30ኛ ጊዜ ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ፤ ለንደን  ውስጥ   በደማቅ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር ፣  እያንዳንዱ አስተናጋጅ ሀገር እንደሚያደርገው ሁሉ ብሪታንያም ፤ አጉልታ ያሳየችው አንዱ ትርዒት የኢንዱስትሪውን አብዮት የሚመለከት እንደነበረ የሚታወስ ነው። በዓለም ታሪክ ውስጥ የኢንዱስትሪው አብዮት እየተባለ የሚጠቀሰው፤ በ 18ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ዓመታት ፣ በብሪታንያ የተከናወነውን ፣ ቴክኖሎጂን መሠረት በማድረግ እየተስፋፋ የመጣውን ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ኩባንያዎችን ግሥጋሴ ነው የሚያሳየው።የኢንዱስትሪው አብዮት ሲባል፣ ከግብርና- መራሽ ኤኮኖሚ፣ ወደ ፋብሪካዎች መሥፋፋትም ሆነ የኢንዱስትሪዎች መቋቋም ፣ በአጠቃላይ  በከተሞች፤ የተገነባውን  ኢንዱስትሪ ነው የሚመለከተው። ይህ ፣ የዓለም የሥልጣኔ  ገጽ እንዲለወጥ ያበቃው የኢንዱስትሪ አብዮት ለመከሠት የበቃው፤ መሻሻልንና ቀጣይነት እያሳየ በመጣ የሥነ ቴክኒክ ግሥጋሴ ሳቢያ ነው።

Bangladeshi workers work in a textile factory on the outskirts of Dhaka, Bangladesh, Wednesday, Feb. 2, 2005.The European Union has decided to give Bangladesh zero tariff entry into its $ 70 billion clothing market from July this year, a move that may boost the country's export to the EU, according to media reports. Bangladesh, a nation of 140 million people, earns three-fourths of its foreign exchange from textile exports. The industry directly employs 1.8 million people and indirectly provides work for about 5 million. (AP Photo/Manish Swarup)
ምስል AP

በእንግሊዝ ሀገር የተጀመረው የኢንዱስትሪው አብዮት ወዲያው ወደ መሃል አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ተዛመተ። ውሎ አድሮም ለመላው ዓለም ተዳረሰ።  ቀስ በቀስ ፤ ግብርናንና ከብት ማርባትን በመተው ፣ ከገጠር ወደ ከተሞች የፈለሰው ህዝብም፤ የኢንዱስትሪ ሠራተኛ ወይም ተቀጣሪ  እየሆነ መጣ። ለዕለትም ሆነ ለዓመት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ፣  ሰው፣  በየቤቱ መሥራቱን እያቆመ፤ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን መግዛቱን  አዲስ ባህል አደረገው ።

በዚያ ዘመን አዲስ የተሠሩ ፤ ወይም በአዲስ ግኝት ከተመዘገቡት መካከል፤ በእንፋሎት ኃይል የሚሠሩ ሞተሮች ፣ ዘመናዊ ማዳወሪያዎች፣ እንዲሁም በውሃ ኃይል የሚሠሩ የዝኀ ማጠንጠኛዎች ፣ እነዚህና የመሳሰሉት፤ የዓለምን ህዝብ አኗኗር ስልት በመስተፋጥናዊ 

ሂደት እጅግ ለውጠውታል። ዘመናዊው ማዳወሪያ፤ በመጀሪያ Thomas Highs በተባለው እንግሊዛዊ ሲሆን የተሠራው፣ በፍርድ ቤት ብዙ ጊዜ ቢያከራክርም ፤ እ ጎ አ ፣ በ 1869 የራሱ የፈጠራ ሥራ ውጤት አድርጎ ያስመዘገበው ፣ ሪቸርድ አርክራይት የተባለው ሌላው የአገሩ ተወላጅ ነው።  

ከአንዱስትሪው አብዮት በፊት፤ ብሪታንያ ሰፊ የጨርቃ ጨርቅ ስራ እንዲስፋፋ ብታደርግም ሠራተኞች ፤ በየቤታቸው በመዳወሪያ ነበረ ዝኃ የሚያዳውሩት። ይሁን እንጂ ይኸው ባህላዊ አሠራር ፣ በሰፊው ለገበያ የሚውል፣ ጨርቃ ጨርቅ ለማቅረብ አመቺ አልነበረምና በጄምስ ሃግሪቭስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው በአንድ ጊዜ ፣ አንድ ብቻ ሳይሆን ፣ 120 ዝሃ የሚያዳውረው ማሺን ፣ የጨርቅ ጨርቅ ኢንዱስትሪውን ገላገለው።

ሌላው፤  አስተዋጽዓ አድራጊ  ዘመናዊው የጥጥ መዳመጫ መሣሪያ ነው። ኤሊ ዊትኒ የተባለው አሜሪካዊ ፣ ነው የሠራው።  ድሮ በባርነት ከባድ ሥራ እንዲያከናወኑ በጌቶቻቸው የተቀጠሩ አሜሪካውያን ነበሩ በእጃቸው፤ ከጧት እስከ ማታ በጥጥ እርሻዎች፤ የጥጥ ፍሬውን ከጥጥ በመለየት ይደክሙ  የነበሩ።  ይሁን እንጂ አዲሱ መሣሪያ ፣ ለኢንዱስትሪው ቀልጣፋ አሰራርና ለምርቱም በሰፊው መዳረስ በጅቷል።

ለጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎችና ለሌሎቹም ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ሰፊ አስተዋጽዖ ያደረገው ሌላው የሥነ ቴክኒክ ውጤት በመገናኛ ረገድ በተለይ ከአውራ ጎዳናዎች ሌላ፣ ሞተሩ፤  በእንፋሎት ኃይል የሚሠራ ባቡር መሠራቱና ሀዲድ መዘርጋቱ ነበር። ይህን ሞተር ለመጀመሪያ ጊዜ ሠርቶ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ያደረገው፣ ጄምስ ዋትሰን የተባለው ነው። የእንፋሎት ሞተሩ፤ በመሠረቱ ባቡሮችን ለማሽከርከር ታስቦ ይሠራ እንጂ፤  በፋብሪካዎችና በማዕድን ማውጫ ጉዳጓዶችም ማሺኖችን ለማሠራት ጠቀሜታ መስጠቱ አልቀረም። Richard Trevithick ፣

ሠረገላዎች፣ጎዳናላይበእንፋሎትሞተርአማካኝነትእንዲንቀሳቀሱያደረገሰውነው።  እጎአ  በ1804 ፣የአንፋሎትኃይልባቡሮችንሀዲድላይእንዲያሽከረክርአስቻለ።የማዕድንኢንዱስትሪእንጂኔርየነበረውታዋቂውጆርጅእስቲፈንሰን፤በ1814 ይበልጥኃይልያላቸውባቡሮችበመሥራቱ፣ባለጥንድሀዲድመዘርጋቱግድሆነ።እናምበኢንግላንድባለሁለትመሥመሮች ወይምጥንድሀዲዶች ለመጀመሪያጊዜ  እጎአበ1825 እና1830  ተሠርተውአገልግሎትመሥጠትጀመሩ።ህዝብለመጀመሪያጊዜየሚመላለስበትንበእንፋሎትኃይልየሚሠራውንባቡርየሠራ፣«የባቡርሐዲዶችአባት» የሚልተቀጥላስምያገኘው፣ጆርጅእስቲፈንሰንነው።

Nachterstedt (Sachsen-Anhalt): Ein Arbeiter kontrolliert am 26.06.2001 im Aluminiumwerk der Alcan Deutschland GmbH in Nachterstedt eine Schere, mit der Alublech zugeschnitten wird. Kunden für die Alubleche aus Nachterstedt sind u.a. führende Automobilhersteller in Europa. Seit der Übernahme durch den kanadischen Konzern im Jahre 1994 sind rund 330 Millionen Mark investiert worden. Wurden vor sieben Jahren 40 000 Tonnen Aluminium verarbeitet, werden es in diesem Jahr 160 000 Tonnen sein. Auch die Beschäftigtenzahl stieg kontinuierlich an: Von 350 im Jahr 1994 auf nunmehr 539. (MGB02-160701)
ምስል dapd

በጀርመንሀገርለመጀመሪያጊዜ፣የስቲፈንሰንባቡርየሚሄድበትን  የሀዲድ  መሥመርየዘረጉት፤ባቡሩንምለመጀመሪያጊዜ፣እ ጎ አ ታኅሳስ 7 ቀን 1835 ዓ ም፣ ከNürenberg ወደFürth  ያሽከረከሩላቸው እንግሊዞች ናቸው። እርግጥ  ከዚያ በፊት ፈረሶች የሚጎቱት ሠረገላ የሚሽከረከርበት ፣ የልዑል ዊልያም ባቡር ሐዲድ ፣ የተሰኘው፤ እ ጎ ኣ, መስከረም 20,1831 ተዘርግቶ ነበር።  እ ጎ አ ሚያዝያ 7 ቀን 1839 የተዘረጋው የመጀመሪያው ረጅም ሀዲድ ፣ ከ ላይፕትዚግ - ድሬስደን የሚያመራው ነው።

በጀርመን ፣ ከሞላ ጎደል አብዛኞቹን ከተሞች የሚያገናኙ የባቡር ሐዲዶች የተዘረጉት፣ እ ጎ አ ፣ ከ 1835 እስከ 1870 ዓ ም ነው።

Fichtelbergbahn Cranzahl-Oberwiesenthal auf dem Viadukt vor Oberwiesenthal, Erzgebirge, Sachsen, Deutschland
ምስል picture-alliance/Bildagentur Huber

ኢትዮጵያ ፤ እንደምኞቷ አልተስፋፋም  እንጂ ፤ የመጀመሪያውን የባቡር ሐዲድ ከፈረንሳይ ጋር በመተባበር፤ ከጂቡቲ ወደ ድሬዳዋ፤ ከዚያም ቆይቶ ወደ አዲስ አበባ እንዲዘረጋ ያደረገች እ ጎ አ በ 1894 ነበር።

ሥነ ቴክኒክ ፤ የቆሰቀቆሰውም ሆነ የቀሰቀሰው የኢንዱስትሪው አብዮት፣ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው፤ የከተሞችን መስፋፋት ያፋጠነ፣ በግብርናና በከብት እርባታ ይኖር የነበረውን  ኅብረተሰብ፣ ወደ ኢንዱስትሪ ሠራተኛነት እንዲዛወር ያደረገ ነው። የኢንዱስትሪው መዛመት፤  አማራጭ የሥራ ዕድል ቢከፍትም፤ አሉታዊ ተጽእኖዎችንም ያስከተለ መሆኑ አይካድም፤  ያኔ ልጆችን በከባድ ሥራ እንዲጠመዱና ጉልበታቸውም እንዲበዘበዝ እስከማድረግ የደረሰው የኢንዱስትሪው አብዮት፣ ዛሬም ድረስ በአንዳንድ በኢንዱስትሪ በመገስገስ ላይ በሚገኙ አገሮች  ሳንክ እንዳለበት ወይም ኢፍትኀዊነትን እያስተናገደ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።

የኢንዱስትሪው አብዮት፣ ከነገሥታት፤ መሣፍንት-መኳንንት ሌላ ፣ በኢንዱስትሪ ባለጸጎች የሆኑ  ፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ሥራ አስኪያጆችን ፣ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ እንዲገኙ ያበቃ ሲሆን ፤ ሠርቶ አደሩ ከዚህ የኢንዱስትሪ ትሩፋት ያን ያክል ሳይደርሰው፤ መደቡን ጠብቆ መጓዝ ሆነ ዕጣ -ፈንታው! በኢንዱስትሪው አብዮት የመጀመሪያ ዓመatት የመንግሥት መርኅ በንግድና ኢንዱስትሪ ጣልቃ አለመግባት የሚል ነበር። ነገር ግን ፤ የሠርቶ አደሮቹ ጉልበት አለቅጥ መበዝበዙ፣ በሠራተኛው መደብ ሰፊ የሆነ የተቃውሞ ንቅናቄ  አስነሣ። በ 1802 እና 1819 ዓ  ም፤ በዛ ያሉ በኢንዱስትሪ የሚሠሩ ልጆችን ደኅንነት አጠባበቅ የሚመለከቱ  የህግ አንቀጾች፣  በፓርላማ በኩል ጸደቁ።

Vintage gramophone © HamMeR #7293934
ምስል Fotolia/HamMeR

የኢንዱስትሪው አብዮት ከምዕራፍ አንድ ወደ ምዕራፍ ሁለት ሲሸጋገር፤ የሥነ ቴክኒክ ግኝቶች ቁጥርም እጅግ እየጨመረ ነበረ የሄደው።

ከባቡር ሃዲድና ባቡር ሌላ አውቶሞቢልም በዚያው በኢንዱስትሪው አብዮት ወቅት ነው የተሠራው። በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ፍጻሜ ለ20ኛው ክፍለ ዘመን ዋዜማ፤ ትኩረት የተሰጠው የአይሮፕላን ሥራ፣  በ 20ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ፣ የኢንዱስትሪውን አብዮት ጠንሳሾች ብቻ አይደለም፣ እ ጎ አ  በ 1903 ዊልበርና ኦርቪል ራይት የተባሉት አሜሪካውያን ወንድማማች በዓለም ውስጥ የመጀመሪያውን አይሮፕላን ሠርተው በማብረር  ፣ መላውን ዓለም ጭምር ነበረ ያስደመሙት። ካናዳዊው  አሌክሳንደር ግራሃም ቤል፣ ስልክ ሠራ፤ ምንም እንኳ በአሁኑ ጊዜ የአጅ ስልኮች የእርሱን የሥራ ውጤት እጅግ እየተሻሙ ቢያስቸግሩም፤ ስልክ ምንጊዜም ከታላላቆች ቀደምት ጠቃሚ የፈጠራ ውጤቶች አንዱ መሆኑ አያጠራጥርም።

Porträt Nikola Tesla
ኒኮላ ቴስላምስል DW / Zoran Simic

በ 1901 (እ ጎ አ) ከአትላንቲክ ማዶ አሜሪካ  ድረስ ፣በኤሌክትሮኒክ መገናኛ ምልክት ሽቦ በሌለው ፣ በቴሌግራፍ መልእክት መለዋወጥ እንደሚቻል ማርኮኒ አሥመሠከረ።  በ 1906 የመጀመሪያው፣ የሰው ድምጽ፣ በድምፅ ሞገድ ፣ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ አልፎ በራዲዮ በተሳካ ሁኔታ እንዲደመጥም አበቃ። በ 1877 ቶማስ አልቫ ኤዲሰን፤ ንግግርም ሆነ ሙዚቃ የሚደመጥበትን ዲስክ (ግራማፎን)ሠርቶ አቀረበ።

ለህንጻ ፤ ለመርከብ ለድልድይና ለመሳሰለው መሥሪያ የሚሆነው ጠንካራ ብረት (እስቲል) መመረት የጀመረው ከ 1850 ዎቹ ዓመታት አንስቶ ነው። በ1870 ፤ በሰር ጆሰፍ እስዋንና በቶማስ አልቫ ኤዲሰን  ኩባንያዎች የጋራ ትብብር  አምፑል ፣ በ 1888 ደግሞ በፈጠራ ውጤቶቹ እጅግ የታወቀው በትውልድ ሰርቢያዊ በዜግነት በኋላ አሜሪካዊ በሆነው  በኒኮላ ቴስላ የኤሌክትሪክ ሞተር መሠራቱ ይታወሳል።

በ 19ኛው ክፍለ ዘመን፤ ለኢንዱስትሪው አብዮት፤ በር የከፈተው ሥነ ቴክኒክና አዳዲስ የፈጠራ ሥራ፣ በ 20ኛው ክፍለ ዘመንና በ 21ኛውም ምን እንደታየበት በሌላ ዝግጅት እንመለስበታለን።  

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ