1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሥደተኞችና የኢጣሊያ ፖለቲከኞች አቋም

ሐሙስ፣ ጥር 21 2001

የላፔዱዛ ከተማ ነዋሪዎች፥ ከንቲባና የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ሐሳቡን ባደባባይ ሰልፍ አዉግዘዉታል።

https://p.dw.com/p/GjXM
ስደተኞቹምስል picture-alliance / dpa

የሜድትራኒያንን ባሕርን አቋርጠዉ ኢጣሊያ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር የኢጣሊያ የሐገር ግዛት ሚኒስቴር አዲስ የማቆያ ጣቢያ ሊያቋቁም አቅዷል።በእቅዱ መሰረት ስደተኞቹ በብዛት ወደ ኢጣሊያ በሚገቡባት ላምፔዱዛ ደሴት በሚቋቋመዉ ጣቢያ ቆይተዉ ማንነታቸዉ እየተጣራ ወደየመጡበት ሐገር ይባረራሉ።ሐሳቡ ግን የሁሉንም ፖለቲከኞች ድጋፍ አላጋኘም።በተለይ የሮማዉ ወኪላችን ተኽለ እግዚ ገብረየሱስ እንደዘገበዉ የላፔዱዛ ከተማ ነዋሪዎች፥ ከንቲባና የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ሐሳቡን ባደባባይ ሰልፍ አዉግዘዉታል።