1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ረሀብ በአዲስ አበባ ተማሪዎች

ዓርብ፣ ጥቅምት 19 2003

ረዺ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ተምህርት ቤት ነው። አንዳንድ ተማሪዎች ረሃብ ያጠቃቸዋል።

https://p.dw.com/p/Ptxe

አንዳንድ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ያንቀላፋሉ፤ ይደክማቸዋል፤ ተዝለፍልፈው ይወድቃሉ። መምህራን እንደሚሉት እነዚህ ተማሪዎች ምግብ ሲያገኙ ወዲውኑ ነፍስ ዘርተው ትምህርታቸውን መከታተል ይጀምራሉ። ተማሪ ዲሪባ ትምህርት ቤት በአብዛኛው ምግብ ሳይበላ እንደሚመጣና ክፍል ውስጥ አንደሚያመው ይናገራል። ተማሪ አሰገደች በረሀብ ምክንያት ትምህርቷን መከታተል እንዳልቻለች ነው የምትገልጸው። መምህርት አስካለ ግዛው ተማሪዎቹ የሚገጥማቸው ችግርን ለመቅረፍ መምህራን ገንዘብ አዋጥተው መመገብ እንደጀመሩ ነገር ግን ቁጥራቸው እየጨመረ በመምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ምክትል ስራ አስፈጻሚና የትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ዕቁባይ አርአያ ችግሩ ተጋንዋል፤ መንግስት የሚችለውን እያደረገ ነው ይላሉ።

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ