1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሩሲያ ጋዟን ዳግም ትለቃለች

ሰኞ፣ ጥር 11 2001

ከዑክሬይን ጋ በገባችዉ ዉዝግብ መዘዝ ለሳምንታት የጋዝ ፍሰቷን አቋርጣ በርካታ የአዉሮጳ አገራትን ግራ ያጋባችዉ ሩሲያ ዳግም አቅርቦቷን ልትጀምር እንደምትችል ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/GcBC
ፑቲንና ቲሞሼንኮ
ፑቲንና ቲሞሼንኮምስል picture-alliance/ dpa

ሩሲያ ቀደም ሲል በዋጋ አልፎም በጋዝ ስርቆት ስትከሳት በከረመችዉ ዑክሬን ላይ የጋዝ ፍሰቱን የሚቆጣጠር ታዛቢ አካል በመስመሮቹ አኳያ የማድረግ እቅድ የነበራት ቢሆንም ለጊዜዉ ግን ካለምንም ተቆጣጣሪ ቧንቧዉን ልትከፍት ትችላለች ነዉ የተባለዉ። በአንዳንድ የአዉሮጳ አገራት የተቋረጠዉ ጋዝ ፍሰት ባስቸኳይ እንዲቀጥል አበክሮ ያሳሰበዉ የአዉሮጳ ኅብረት የሩሲያና የዑክሬን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከተፈለገዉ ስምምነት የሚያደርሳቸዉን ዉይይት ማካሄዳቸዉን ደግፏል። ለጋዙ መቋረጥ የቀረበዉ ሳቢያና የተከተለዉ ዉጤት ግን እንዳሳሰበዉ አልሸሸገም።