1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ርምጃ በሀሰተኛ መረጃ አቅራቢዎች ላይ

ዓርብ፣ ሰኔ 14 2011

በአማራ ክልል በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጥረው ሲሠሩ የነበሩ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ተወሰደ፡፡ በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ በተደረገ የማጣራት ሥራ በክልሉ ከ500 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ሲሠሩ እንደነበር የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አመልክቷል፡፡

https://p.dw.com/p/3KqBC
Äthiopien | Amhara Regionalregierung Büro für öffentlichen Dienst und Personalentwicklung
ምስል A. Mekonnen

ከ500 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ሲሠሩ ነበር

በአማራ ክልል በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጥረው ሲሠሩ የነበሩ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ተወሰደ፡፡ በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ በተደረገ የማጣራት ሥራ በክልሉ ከ500 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ሲሠሩ እንደነበር የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አመልክቷል፡፡ በዋናነት የሀሰተኛ ማስረጃው በትምህርት የብቃት ማረጋገጫ፣ በመንጃ ፈቃድ፣ በሥራ ልምድና በሌሎችም ዘርፎች የተገኙ እንደሆነ በኮሚሽኑ የሰው ሀብት ሥራ አመራር፣ አፈፃፀም፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ ዓበይነህ ወርቁ ተናግረዋል፡፡ የሀሰተኛ ማስረጃዎቹን በጥቆማ፣ በነፃ የሰልክ ጥቆማ በሃሰብ መስጫ ሳጥንና በሌሎች ስልቶች ተሰብስበው የማጣራት ሥራ ተከናውኗል ብለዋል። ከ8ኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ድረስ ሃሰተኛ ማስረጃ ከማኅደራቸው ጋር ያያዙ ሰዎች መገኘታቸውን አስታውሰው፣ የተገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ ከአማራ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በቅንጅት በመስራት መረጃውን መሰረት በማድረግ 547 ሠራተኞች ከሥራ ተሰናብተው 60ዎቹ መሳረጃቸው እንደገና ተመርምሮ ችግር የሌለበት በመሆኑ ወደሥራቸው ተመልሰዋል ነው ያሉት፡፡ ወደፊትም ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ቀጣሪ አካላት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲደርጉ አቶ ዓባይነህ አሳስበዋል፡፡ 

Äthiopien | Abayneh Worku | Amhara Regionalregierung Büro für öffentlichen Dienst und Personalentwicklung
ምስል A. Mekonnen

ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ