1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ርእሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲ የአፍሪቃ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ኅዳር 15 2008

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በአፍሪቃ የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬ በኬንያ ጀመሩ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ናይሮቢ ሰገቡም ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል።

https://p.dw.com/p/1HCbU
Kenia, Papst Franziskus besucht Kenia
ምስል Reuters/G. Tomasevic

[No title]



የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርእሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲ የመጀመርያ የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉን ዛሬ በኬንያ ጀመሩ። ርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስን ያሳፈረ አዉሮፕላን ወደ ኬንያ መዲና ናይሮቢ ማምራቱን የብዙኃን መገናኛዎች መጠገብ የጀመሩት ዛሬ ከቀትር በፊት ነበር። የ 78 ዓመቱ ትዉልደ አርጀንቲናዊ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ርእሰ ሊቃነ-ጳጳሳት በኬንያ የሁለት ቀናት ቆይታ ካደረጉ በኋላ ወደ ዩጋንዳ እንደሚያመሩ ተመልክቶአል። ከዝያም በመጨረሻ መካከለኛ አፍሪቃ ሪፐብሊክን ጎብኝተዉ የፊታችን ሰኞ የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉን አደንደሚያጠናቅቁ ተዘግቦአል። በኬንያ ቆይታቸዉም ከተመድ የአካባቢ ጥበቃ መርሃግብር በተጨማሪ ከናይሮቢ ወጣ ብሎ የሚገኘዉን እና አንድ መቶ ሺህ የሚሆኑ ሰዎች የሚኖሩበትን ካንጌሚ የተባለ ጎስቋላ መንደር ይጎበኛሉ። አፍሪቃ 180 ሚሊየን የካቶሊክ እምነት ተከታዮች እንደሚኖሩባት የጀርመን የዜና ወኪል ዘግቧል።
ኬንያ በተለይ መዲና ናይሮቢ ርእሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲን ለመቀበል ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች መሆንዋን የናይሮቢዉ ወኪላችን ፋሲል ግርማ በስልክ ገልጾልናል።

Kenia, Papst Franziskus besucht Kenia
ምስል Reuters/G. Tomasevic


ፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ