1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላለፉ  

እሑድ፣ ታኅሣሥ 16 2009

የገና ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የጎሮጎሮሳዉያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተለዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ዘንድ ዛሬ በመከበር ላይ ነዉ። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራት የሐይማኖት መሪዎችና ፖለቲከኞች ለየተከታዮቻቸዉ መንፈሳዊና ዓለማዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/2UrKB
Vatikanstadt Petersdom Papst Franziskus - Segen Urbi et Orbi
ምስል Reuters/A. Bianchi

 

የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓመታዊዉ እና ባህላዊዉ የገና ንግግራቸዉ በሶርያ እየተካሄደ ስላዉ አሰቃቂ የሰብዓዊ እልቂት ላይ ነበር ያተኮሩት። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደተናገሩት በሶርያ የሲቪል ማኅበረሰቡ አስቸኳይ ርዳታ ይሻል፤ የርስ በርስ ጦርነት በተዘፈቀችዉ ሃገር በሶርያ የሲቪል ማኅበረሰቡ ላይ እየተካሄድ ያለዉ የሰብዓዊ ጥሰቶች ይቁሙ ሲሉ በቫቲካን ቅዱስ ፔተር አደባባይ ላይ ለተሰበሰበዉ ወደ 40,000 የሚጠጉ ምዕምናን በታደሙበት ተናግረዋል።  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በአዉሮጳ በተለያዩ ጊዜያቶች በተፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች የተገደሉ ሰለቦችንም በፀሎታቸዉ አስበዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኡርቢ ኤታ ኦርቢ» «ለከተማዉና ለዓለም» የተሰኘዉን ዓመታዊ የገና መልእክት አስተላልፈዋል።

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ