1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ እና በባህርዳር መታቀዱ

Merga Yonas Bulaማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2008

በኦሮሚያ ክልል ባለፈዉ ሕዳር የተጀመረዉ የአደባባይ ሰልፍና ተቃዉሞ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። የመንግሥት የፀጥታ ሐይላት ተቃዉሞዉን ለማስቆም በወሰዱት የሐይል እርምጃም በርካታ ሰዎች መሞት፤ መቁሰል፤ መታሰራቸዉ፣ በርካታ ሰዉ እየተሰደደ መሆኑ ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1JaSR
Oromo Proteste in Äthiopien
ምስል Oromia Media Network

[No title]

በመጭዉ ቅዳሜ ደግሞ አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ሰላማዊ ሠልፍ ለማካሄድ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጥሪ እየተደረገ ነዉ። <<ላለፉት ዘጠኝ ወራት በየአንድንዱ ቀን ሁለት ሰዉ እየተገደለ ነዉ።» የምሉት የፖለትካ ተንታኝ እና የሰዉ መብት አቀንቃኝ አቶ ጃዋር መሃመድ «አሁንም ተቃዉሞዉ በሃራርጌ፣ በሸዋ፣ በአርሲ እና በቦራና ቀጥለዋል» ይላሉ። ለሰላማዊ ሰልፍን ለማካሄድ ለፌዴራሉም ሆነ ለክልሉ መንግስት ድብዳቤ ተልኮ በኦሮሚያ በኩል አዉንታዊ አመለካከት እንዳለ አቶ ጃዋር ይናገራሉ።

ይሁን እንጅ ዶቼ ቬሌ በሁለቱም የመንግስት አካላት በኩል ለማነጋገር ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

ቅዳሜ ይካሄዳል የተባለዉን ሰላማዊ ሰልፍ ያዘገጀዉ አካል ማን እንደሆነና የሰላማዊ ሰልፉ አላማ ምን ነቸዉ ተብሎ አቶ ጃዋር ስጠየቁ የተደራጀ አካል ባይኖርም የ#OromoProtests የሰዉ መብት አቀንቃኝ እንደሆኑ ይናገራሉ።

የቅዳሜዉ ሰልፍ ዓላማ የታሰሩት የፖለትካ እስረኞች <<በአስሸኳይ>> እንዲፈቱ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ የሚደረገዉ <<መጠነ ሰፊ ግድያ እንዲቆምና ገዳዮች ለፍርድ እንድቀርቡ>>፣ ኦሮሚያ ራሱን የማስተዳደር መብቱ እንድጠበቅለት እና የህዝቦች መብት እንዲከበር ለመጠየቅ እንደሆነ አቶ ጃዋር ያብራራሉ።


እሁድ ቀን ደግሞ በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ላይ ሰማያዊ ፓርት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን የፓርቲዉ የምክር ቤት አባል አቶ ስለሺ ፋይሳ ለዶቼ ቬሌ አረጋግጠዋል። በአገርቱ በተለያዩ ቦታዎች እየተካሄደ ባለዉ ተቃዉሞ የሚነሱ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ ስላላገኙ ጥያቄዉ ወደ <<ስረዓት ለዉጥ>> ጥያቄ እየመጣ ነዉ ይላሉ አቶ ስለሺ።

ለበለጠ መረጃ አዉዲዮዉን ያዳምጡ።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ