1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተጨማሪ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለደቡብ ሱዳን፤

ሰኞ፣ ነሐሴ 2 2008

ደቡብ ሱዳንን ለማረጋጋት ተጨማሪ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲላክ ዩናይትድ ስቴትስ ሃሳብ አቀረበች። ዋሽንግተን ለተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት ባቀረበችዉ ሃሳብ አራት ሺህ የሚሆን ጠንካራ የሰላም አስከባሪ ኃይል ነዉ ወደጁባ እንዲላክ የጠየቀችዉ።

https://p.dw.com/p/1JdbR
Südsudan UN denken über Verstärkung von Unmiss nach
ምስል Reuters/A. Ohanesian

[No title]

የሀገሪቱ የሽግግር የአንድነት መንግሥት የማይተባበርም ከሆነ የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ሊጣልበት እንደሚችልም አስጠንቅቃለች። የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት ማለትም ኢጋድ አባል ሃገራት ተጨማሪ ጦር ለመላክ ጥያቄ አቅርበዉ፤ ከጁባም አዎንታዊ ምላሽ ተገኝቷል። ሆኖም የፕሬዝደንት ሳንቫ ኪር መንግሥት የሠራዊቱን ብዛት እና የሚሰማራበትን አካባቢም ለመወሰን እንደሚመክር አመልክቶ ነበር። በጉዳዩ ላይ ናይሮቢ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማን በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

ፋሲል ግርማ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ