1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰማያዊ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄደው ውይይት 

ሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2010

አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደው የአመራር ለውጥ የሕዝቡ ትግል ውጤት እንደሆነ እና ሕዝቡ የሚፈልገዉን ለውጥ ለማምጣት ማንንም መጠበቅ እንደሌለበት ተገለጸ። ይህ የተገለፀው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባካሄዱት የውይይት መድረክ ነው።

https://p.dw.com/p/2wX5I
Demonstration der Semayawi-Partei in Addis Ababa Äthiopien 22.09.2013
ምስል DW

የሰማያዊ ፓርቲ ውይይት 

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ጊዜያት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊ ዉይይቶች እያካሄደ መምጣቱ ይታወቃል። የዚህ ተከታታይ መርሃግብር አካል የሆነና አሁን በአገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥ እና የወደፊት ሁኔታን በተመለከተ ባሳለፍነው የሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ዕለት አባላት ደጋፊዎቹ የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ፓርቲው አከናዉኗል። የፓርቲው ሊቀመምበር አቶ የሺዋስ አሰፋ፤ በወቅቱ በተደረገው ውይይት ለውጥ ለማምጣት ሕዝቡ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚኖርበት አፅንኦት መሰጠቱን አመልክተዋል።
በዉይይት መድረኩ ላይም የመወያያ ጽሑፍ ቀርኗል። ፅሑፉን ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲ መምህር እና የአምደ መረብ ፀሐፊው አቶ ስዩም ተሾመ፤ አሁን በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ የሕዝቡ ትግል ውጤት ነው ይላሉ።
ፓርቲዉ የሚያዘጋጃቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ የውይይት መድረኮች ቀጣልነት እንዳላቸውም ከአቶ የሺዋስ አሰፋ ማብራሪያ ለማወቅ ተችሏል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ሸዋዬ ለገሠ