1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰማያዊ ፓርቲ ተፈቺዎችን ለመቀበል ተዘጋጅቻለሁ አለ

ሰኞ፣ የካቲት 5 2010

ሰማያዊ ፓርቲ ከእስር የሚፈቱ ፖለቲከኞችን ለመቀበል መዘጋጀቱን አስታውቋል። ፓርቲው በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል

https://p.dw.com/p/2sYVt
Äthiopien Oppositionspartei Blue Party PK
ምስል DW/Getachew Tedla HG

የሰመያዊ ፓርቲ መግለጫ

ኢትዮጵያውያን ከእስር ይፈታሉ የተባሉ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን በጉጉት እየጠበቁ ነው። በግንቦት ሰባት አባልነት ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት እማዋይሽ አለሙ እና የሽብር ክስ የቀረበባት ወጣት ሴና ሰለሞን  "ለቅድመ ፍቺ ሥልጠና ከቃሊቲ ማረሚያ ወጥተዋል" ሲል ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ በግል የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል። አቶ ማሙሸት አማረ፣ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔርም ከሚፈቱት መካከል ናቸው የሚሉ መረጃዎች በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ታይተዋል። ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌ ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እና የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የቀረበላቸውን የይቅርታ መጠየቂያ ደብዳቤ አንፈርምም ማለታቸው አይዘነጋም። ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ከእስር የሚፈቱ ፖለቲከኞችን ለመቀበል መዘጋጀቱን አስታውቋል። ፓርቲው በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ