1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰሜን አፍሪቃ የአሸባሪዎች ምሽግ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 9 2007

እራሱን «እስላማዊ መንግሥት» እያለ የሚጠራው ቡድን ከሊቢያ አልፎ በመላው ጎረቤት ሃገራትም ስጋት መሆኑ ተነግሯል። ሊቢያ ጠንካራ መዓከላዊ መንግሥት አጥታ በተከፋፈሉ የጦር አበጋዞች መመራቷ ቡድኑ የሽብር ተግባሩን በስፋት ለማራመድ አመቺ ሁኔታን ፈጥሮለታል። ዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪ ቡድኑን በአው አልባ አውሮፕላኖች ልትደበድበው አቅዳለች።

https://p.dw.com/p/1FyUw
Libyen Kampf gegen IS
ምስል Mahmud Turkia/AFP/Getty Images

[No title]

ሊቢያ በእርስ በርስ ጦርነት ተጠምዳለች። የመፈረካከስ ስጋት ካጠላባትም ሰነባብታለች። እራሱን «እስላማዊ መንግሥት» እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን በባሕር በበረሃዋ ይርመሰመስባታል። ያም ብቻ አይደለም አሸባሪ ቡድኑ ከሊቢያ ምሽጉ ወጥቶ በጎረቤት ሃገራት ላይ አደጋውን ጋርጧል። ዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ በራሪ ጢያራዎቿን በሊቢያ ድንበር አስፍራ አሸባሪዎቹን ከዓየር ላይ ለመደብደብ ማቀዷ ተዘግቧል። የዶይቼ ቬለዋ ዲያና ሆዳሊ ያቀረበችውን ዘገባ፤ ይልማ ኃይለሚካኤል እንደሚከተለው አቀናብሮታል።

ዲያና ሆዳሊ/ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ