1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በርካታ ሀገሮች የቦምቡ ሙከራ አስግቷቸዋል

እሑድ፣ ነሐሴ 28 2009

ዓለም በሰሜን ኮሪያ የሐይድሮጅን ቦምብ ሙከራ ጭንቅ ጥብብ ብሏት ውላለች። የሰሜን ኮሪያ ዜና አገልግሎት በአኅጉር አቋራጭ ሚሳይል ላይ ሊጠመድ የሚችል የሐይድሮጅን ቦምብ ሙከራው "ስኬታማ ነበር" ሲል ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/2jHib
Fußgänger in Tokio schauen einen Bericht über den erfolgreichen Wasserstoffbombentest in Nordkorea
ምስል Reuters/T. Hanai

ከጃፓን እስከ አሜሪካ ከበርሊን እስከ ፓሪስ የሙከራው ዜና ሲወገዝ ውሏል።  የተለያዩ የሥነ-ምድር ምርምር ማዕከላትም  በሰሜን ምሥራቅ ሰሜን ኮሪያ ሰው ሰራሽ የምድር መንቀጥቀጥ መፈጠሩን መመዝገባቸውን ገልጠዋል።የደቡብ ኮሪያ ጦር ሙከራውን እየመረመርኩ ነው ሲል ጃፓን በበኩሏ የኪም ጆንግ ኡን ሀገር ሙከራውን ለማድረጓ እርግጠኛ ነኝ ብላለች። የአሜሪካ የሥነ-ምድር ጥናት ማዕከል ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደም የኑክሌር ፍንዳታ ባካሔደችበት ቦታ አቅራቢያ በሬክተር ስኬር መለኪያ 6.3 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጧል። ሰሜን ኮሪያ አደረኩት ካለችው የሐይድሮጅን ቦምብ ሙከራ በኋላ የቀጠናውን አገራት ጨምሮ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሥጋት ተጭኗቸዋል።የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒሥትር ሺንዞ አቤ የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ መርኃ-ግብር ከባድ እና አስቸኳይ ሥጋት ፈጥሯል ብለዋል። የሰሜን ኮሪያ የአሁኑ ሙከራ በጃፓን ሰማይ ላይ ሚሳይል ከተኮሰች ከጥቂት ቀናት በኋላ የተደረገ ነው። የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳን ኤማኑዌል ማክሮ ሙከራውን በፅኑ ኮንነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስቸኳይ እርምጃ እንሲወስድ ጥሪ አቅርበዋል። ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት በበኩሉ የሰሜን ኮሪያን ሙከራ "የሚያሳዝን ድርጊት" ብሎታል። ሁሉም ወገኖች እንዲረጋጉ ጥሪ ያቀረበችው ሩሲያ ቀውሱን ለመፍታት ሁነኛው መንገድ መነጋገር ብቻ ነው ብላለች። ቻይና የንግድ ሸሪኳ የተሳሳተ እርምጃዋን እንድታቆም ጥሪ አቅርባለች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ማኅበራዊ ድረ-ገፃቸው ባሰፈሯቸው ተከታታይ መልዕክቶች ሰሜን ኮሪያ በቃላትም ይሁን በድርጊቷ ጠብ ጫሪነቷን ቀጥላለች ሲሉ ወቅሰዋል።  

Kim Jong Un Nordkorea
ምስል picture-alliance /dpa/KRT via AP Video
Nordkorea Kim Jong Un bei Besuch einer Fabrik für Nuklearwaffen
ምስል Reuters/KCNA

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ