1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰብአዊ መብትና ያልተቋረጠው የብሔረሰቦች ስሞታ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 27 2006

በአፍሪቃም ሆነ በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ሃገራት እንደሚታየው ሁሉ ፤ ኢትዮጵያም በአያሌ ዘመናት ታሪኳ፤ በዛ ያሉ የተለያዩ ብሔር-ብሔረሰቦችን አቅፋ የኖረችና፣ የምትገኝ ሃገር ናት ። የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት ፣ በህገ መንግሥትም ሆነ በመገናኛ ብዙኀን

https://p.dw.com/p/1Al6N
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ተደጋጋሞ የተወሳውና በመወሳትም ላይ ያለው አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረ 22 ዓመት ከመንፈቅ ገደማ በሆነው የ ኢ ህ አ ዴ ግ ዘመነ- መንግሥት ነው። የብሔረሰቦችን መብት በተመለከተ ቃልና ተግባር እስከምን ድረስ ተጣጥመዋል?። መሠረታዊው ግለሰባዊም ሆነ ማሕበረሰባዊው የመብት ይዞታ እንዴት ነው? ከተለያዩ አካባቢዎች ወደዚህ ራዲዮ ጣቢያ የሚላኩ የ SMS ና የድምፅም መልእክቶች እንደሚጠቁሙት፣ የመብት ጥያቄ እንደቀጠለ ነው። ለምሳሌ ያህል የቁጫና የሸካ ብሔረሰቦች የሚያቀርቡትን ስሞታ መጥቀስ ይቻላል። መጥቀስ ብቻ ሳይሆን፣ ባለሙያዎች ይወያዩበት ዘንድ ለዛሬ የውይይት ርእሳችን አድርገነዋል።

ተክሌ የኋላ