1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የአሜሪካን ህግ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 6 2009

ህጉ በሙስና እና በሰብዓዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ተጠያቂ በሆኑ ላይ የአሜሪካን የይለፍ ፈቃድ ቪዛ እገዳ እና የተለያዩ ማዕቀቦችን በቀላሉ መጣል ያስችላል ።

https://p.dw.com/p/2UKai
USA Kapitol
ምስል picture-alliance/AP Images

Beri. Washington (U.S Congress Passes Human Right Accountability Act) - MP3-Stereo

የዩናይትድ ስቴትስ  ኮንግረስ የተለያዩ ሀገራት ባለሥልጣናት እና ግለሰቦች በዜጎቻቸው ላይ ለፈፀሙት በደል ተጠያቂ የሚሆኑበትን ህግ አጸደቀ ።  ህጉ በሙስና እና በሰብዓዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ተጠያቂ በሆኑ ላይ የአሜሪካን የይለፍ ፈቃድ ቪዛ እገዳ እና የተለያዩ ማዕቀቦችን በቀላሉ መጣል ያስችላል ። በወንጀሎቹ ተጠያቂ የሆኑ ፣በአሜሪካ የሚገኝ ንብረታቸውን መውረስ የሚያስችል እና ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያደርግ ነውም ተብሏል ህጉ ።እርምጃውን በጎ ያሉት አንድ የህግ ባለሞያ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ህጉ መጽደቁ ህዝቦችን የሚበድሉ ባለሥልጣናት ሁለቴ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል ብለዋል ። አንድ የሰብዓዊ መብቶች ተማጋች ደግሞ በወጣው ህግ መደሰታቸውን ገልጸዋል ። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል  ።
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ 
ሸዋዬ ለገሠ