1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰዎች ለሰዎች እና የቀጠለዉ ተቃዉሞ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 4 2005

ኢትዮጵያ ዉስጥ በግብረሠናይ አስተዋፅኦዉ ተቀባይነት ያተረፈዉ ሰዎች ለሰዎች የተሰኘዉ ድርጅት ለዓመታት በአዉሮጳም መልካም ስም ይዞ ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በአሁኑ የድርጅቱ አመራር ላይ ከድርጅቱ ነባር ለጋሾች ጠንካራ ወቀሳና ተቃዉሞ እየቀረበ ነዉ።

https://p.dw.com/p/18ntW
ምስል picture-alliance/dpa

ለጋሾቹ ተፈጽሟል ያሉትን የገንዘብ ብክነት በመጥቀስ ጉዳዩ አደባባይ ከወጣ ወዲህም «በመዋጮ ላይ የተፈፀመ ቅሌት» በተሰኘ ድረገፅ ለድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ለወይዘሮ አልማዝ በም ከአንድ ሺ በላይ ደብዳቤዎች መላካቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ድርጅቱን በገንዘብ የሚረዱት ወገኖች ስራ አስኪያጇ ሥልጣናቸዉን እንዲለቁ፤ ለድርጅቱ የሰጡትም ገንዘብ እንዲመለስላቸዉ ቅሬታቸዉን ባዘለዉ ደብዳቤ መጠየቃቸዉ ተገልጿል። ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ የሚሹም አሉ። ከዚህ ቀደም ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ ወይዘሮ አልማዝ ወጪና ገቢዉ በዉጭ ኦዲተሮች እንደሚመረመር በመግለፅ ክሱን አጣጥለዋል። የዶቼ ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ በማኅበራዊ መገናኛዎችና በመገናኛ ብዙሃን የተጠናከረዉን ዘመቻ አስመልክቶ ከዋና ለጋሾቹ አንዱን አነጋግሯል። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል ባጭሩ እንደሚከተለዉ አሰባስቦታል።

ሉድገር ሻዶምስኪ/ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ