1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳንና የጀርመናውያኑ ጦር ታዛቢዎች ተልዕኮ

ዓርብ፣ መስከረም 19 1999

ስለሱዳን የርስበርስ ጦርነት የሚሰማ ሁሉ ቶሎ ትዝ የሚለው --- >;

https://p.dw.com/p/E0i2
የጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት
የጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤትምስል AP
በምዕራባዊው የሀገሪቱ ከፊል የቀጠለው የዳርፉር ውዝግብ ነው። ይሁንና፡ በደቡባዊው የሀገሪቱ ከፊልም ከመንግሥቱ ጦር ጋር በተካሄደው የሀያ አንድ ዓመት የርስበርስ ጦርነት ወደ ሁለት ሚልዮን ሰው መሞቱና አራት ሚልዮን ደግሞ መሰደዱ ሊዘነጋ አይገባም። ለዚሁ አካባቢ እአአ በ 2005 ዓም የተደረሰውን የተኩስ አቁም ደምብ የተ መ ድ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ይቆጣጠረዋል። በዚሁ ሠራዊት ውስጥ ሠላሣ ስድስት የጀርመናውያን የጦር ታዛቢዎች ተሳታፊዎች ሲሆኑ፡ ተልዕኮዋቸው በሁለት ሣምንታት እንዲራዘም የሀገራቸው ፌዴራዊ ምክር ቤት ውሳኔ ትናንት አሳልፎዋል።