1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሲና በረሀ የታገቱት የኤርትራ ስደተኞች እና የአውሮፓ ፓርላማ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 13 2003

ሲና በረሀ ውስጥ እንደታገቱ ከሚገመተው አብዛኛዎቹ ከኤርትራ ናቸው ከሚባሉ 250 የሚደርሱ ስደተኞች 8 ቱ ሳይሞቱ እንዳልቀረ የስደተኞች ካውንስል የተባለ ድርጅት አስታወቋል ። ድርጅቱ እንደሚለው ቀሪዎቹ ታጋቾች የሚገኙበት ሁኔታም አሳዛኝ ነው ።

https://p.dw.com/p/QiZr
ሲና በረሀምስል picture-alliance / dpa

በሌላም በኩል የግብፅ መንግስት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ጠይቋል ። ፓርላማው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአካባቢው የሚካሄደው ሀገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና በድንበር ላይ የሚገደሉት ስደተኞች ጉዳይ እንደሚያሳስበው አስታውቆ ግብፅ ሲና በረሃ የታገቱትን የኤርትራ ስደተኞችን ለማስለቀቅ መንግስት ጥረት እንዲያደርግ የሚያሳስብ ውሳኔ አሳልፏል ። በመንግስታቱ ድርጅት የስደተኛ ቻርተር መሰረት ፣ መንግስት ለስደተኛ ጥበቃ ሊያደርግ እና ተገንም ሊሰጥ እንደሚገባም ፓርላማው በውሳኔው አስታውቋል ። ውሳኔውን መነሻ በማድረግ የብራሰልሱ ዘጋቢያችን የፓርላማውን የልማት ኮሚሽነር እንዲሁም የስደተኞች ካውንስል ቃል አቀባዮችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ