1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሲየራ ልዮን እና የጦር ወንጀለኞችዋ

ቅዳሜ፣ የካቲት 21 2001

በስብዕና አንጻር እና የጦር ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ ከፍርድ ሊያመልጥ እንደማይገባ ልዩ የሲየራ ልዮን ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከጥቂት ቀናት በፊት ባሳለፈው ብይን አስገነዘበ።

https://p.dw.com/p/H3op
ሶስቱ ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠባቸው የተባበረው ዓብዮታዊ ግንባር መሪዎች
ሶስቱ ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠባቸው የተባበረው ዓብዮታዊ ግንባር መሪዎችምስል AP

ፍርድ ቤቱ ሶስት የቀድሞ የሲየራ ልዮን የተባባረው ዓብዮታዊ ግንባር የተሰኘው ዓማጽያን ቡድን መሪዎች በሀገሪቱ የርስበርስ ጦርነት ጊዜ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂዎች መሆናቸውን አራጋግጦ በቅርቡ ተገቢውን የቅጣት ብይን እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መልካም መሆኑን ቢያመለክትም፡ ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ብዙ የጦር ወንጀል ተጠርጣሪዎች አሁንም በነጻ በመዘዋወር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው ገልጾዋል።

AI/RTRE

AA/HM