1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳምንታዊዉ ስፖርት

ሰኞ፣ ጥር 26 2006

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ከጥር ከነገ አንስቶ እስከፊታችን ዓርብ፤ በ 126ኛው ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ፣ በክብር እንግድነት በመገኘት እንደሚሳተፉ ተነገረ። ስብሰባው የሚካሄድባት ከተማ ፣ የክረምት ኦሊምፒክ እስፖርት ውድድር የምታዘገጀው የሩሲያ ከተማ ሶቺ ናት።

https://p.dw.com/p/1B2Az
ምስል Getty Images

ባን ኪ ሙን፤ ስፖርትና ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፤ ለኅብረተሰቡ በሚያበረክቱት ድርሻ መጠን ላይ በሚካሄደው ክርክር ተሳታፊ ይሆናሉ።
ለአካል ብሎም ለመንፈስ ጥንካሬ የሚበጀው ስፖርት ፣አንዳንድ እስፖርተኞች፤ በጥረትም ሆነ ችሎታ ሳይሆን አስነዋሪና ጎጂ በሆነ መልኩ በጉልበት ሰጪ መድኃኒት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ራስ ምታት ሆኖ መቆየቱ የሚታበል አይደለም። ምርመራውም ሆነ ክትትሉ ተጠናክሮ ቢቀጥልም፤ ሥጋቱ አልተወገደም። የሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ ፣ ለጡንቻ ጥንካሬ የሚሰጥ አዲስ ሰው ሠራሽ ጉልበት ሰጪ ቅመም ስለመገኘቱ
ማብራሪያ ሰጥቷል። ይህን ለመገንዘብ የበቁት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፤ ጀርመናዊው ቶማስ ባህ፤ በፀረ ጉልበት ሰጪ ቅመማት ምርምር ላይ ያተኮረው ድርጅት ምንጊዜም ተከታትሎ እንደሚያከሽፈው ጸኑ እምነት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ወደ ሳምንታዊው የእስፖርት ዝግጅታችን እናምራ

Sotschi Berge Panorama
ምስል picture-alliance/dpa/Mihail Mokrushin/RIA Novosti

ሐና ደምሴ---

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ