1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ሳዑዲ ድንበር የሚገኙ ከ 500 በላይ እስረኞች ድረሱልን እያሉ ነዉ 

ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 2011

ከ 500 በላይ የሚሆኑና በየመን እና በሳዉዲ ድንበር አቅራብያ በሚገኝ እስርቤት ያሉ ኢትዮጵያዉያን አቤቱታችን ለመንግሥት ንገሩልን ሲሉ ገለፁ። በህክምና እጦት እየተሰቃየን ነዉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን እስረኞች በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄ የተቀነሰልን የእስር ጊዜ ተግባራዊ አልሆነምም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3Lvo2
Äthiopien äthiopische Flüchtlinge Rückkehrer im Addis Ababa IOM Transit Center
ምስል IOM Ethiopia

በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄ የተቀነሰልን የእስር ጊዜ ተግባራዊ አልሆነም

ከ 500 በላይ የሚሆኑና በየመን እና በሳዉዲአረብያ ድንበር ላይ በሚገኝ እስርቤት የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን አቤቱታችን ለመንግሥት ንገሩልን ሲሉ ገለፁ። በእስር ቤት የሚገኙት የእፅ አዛዋዋሬ ኢትዮጵያዉያን እስረኞች በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄ የተቀነሰልን የእስር ጊዜ ተግባራዊ አልሆነም፤ ታማሚ የሆነዉም የሕክምና ክትትል ተነፍገናል ሲሉ ገለፁ። ሳዉዲ አረብያ የሚገኘዉም የኢትዮጵያ ኤንባሲም ለዚህ ችግር መፍትሄ ሊያሰጠን ይችል ነበር ሲሉም ነዉ የተናገሩት። በሌላ በኩል ሳዉዲ አረብያ ዉስጥ በአደንዛዥ እፅ ዝዉዉር የሚከሰሱ ሰዎች ከአንድ አካባቢ የመጡ  ሰዎች ናቸዉ፤ የተከበረዉን ኢትዮጵያዊ ስማችንንም አጎደፉብን ሲሉ በበኩላቸዉ ቅሬታቸዉን አሰምተዋል።   በጉዳዩ የኢትዮጵያ ኤንባሲን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።(ፎቶ ከክምችት) 


ነብዩ ሲራክ 

አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሰ