1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለትግራይ የርዳታ ማጓጓዣ የሰብአዊ ተቋማት አስተያየት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 20 2013

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ወቅታዊው የሰብአዊ ሁኔታ ስጋት የሚፈጥር በመሆኑና ባሉት ተግዳሮቶች የተነሳ በልሉ ካለው የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎት ጋር በሚጣጣም መልኩ ርዳታ ማቅረብ አለመቻሉን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊና የአስቸኳይ ርዳታ ማስተባበሪያ አመለከተ። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ መንገዶች እንዲከፈቱም ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/3zWA0
Äthiopien Bürgerkrieg Tigray
ምስል BAZ RATNER/REUTERS

ርዳታ ተሟጦ ማለቁን ዐስታውቀዋል

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ወቅታዊው የሰብአዊ ሁኔታ ስጋት የሚፈጥር በመሆኑና ባሉት ተግዳሮቶች የተነሳ በልሉ ካለው የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎት ጋር በሚጣጣም መልኩ ርዳታ ማቅረብ አለመቻሉን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊና የአስቸኳይ ርዳታ ማስተባበሪያ አመለከተ። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ መንገዶች እንዲከፈቱም ጠይቋል።

ካለፈው ሰኔ መጨረሻ ወዲህ 320 የሰብአዊ ድጋፍ ርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ትግራይ ማድረስ መቻሉን የገለጸው የማስተባበሪያው ደቡብና ምስራቅ አፍሪቃ ክፍል ጽ/ቤት፤ ሚሊዮኖች በተራቡበት በክልሉ አሁን 450 ሺህ ህዝብ ለከፋ ረሐብ ተዳርጓልም ብሏል።

ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የቃጠናው የሰብአዊ ተቋማሙ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ሳቪያኖ አብሪዩ እንደሚሉት የርዳታ ማጓጓዣ ሂደቱን እያጋጠሙ ያሉት ተግዳሮቶች ካልተፈቱ በሰሜን ኢትዮጵያ 1.8 ሚሊየን ህዝብ ለአስከፊ ርሃብ ሊዳረጉ ይችላሉ።

የአፋር እና የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት በፊናቸው አልፎ አልፎ በጦርነቱ ሳቢያ ከሚፈጠረው መስተጓጎል ውጭ በአፋር በኩል ወደ ትግራይ የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፎችን የማድረሱ ጥረት እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ከቀናት በፊት ድርጅታቸው፣ አጋሮቹ እና ሌሎች ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች በትግራይ በሚገኙ መጋዘኖች ያከማቹት የምግብ ርዳታ ተሟጦ ማለቁን አስታውቀው ህወሓት ወደ ሌሎች ክልሎች የሚፈጽመው ጥቃት ግጭት እና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሥቃይ ያራዝመዋል ማለታቸው አይዘነጋም።

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ