1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለየመን የመከረው የአውሮጳ ኅብረት

ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2011

በየመን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትናንት ብራስልስ ውስጥ የመከሩት የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች ሰላም ማስፈን የሚቻለው በድርድር መኾኑን ገለጡ። የየመን ግጭት ለማስቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጀመረው የሰላም ጥረትንም እንደሚደግፉ አበክረው ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3FJm4
Großbritannien London - EU Flagge vor dem Parlament
ምስል picture-alliance/NurPhoto/A. Pezzali

በየመን ግጭት ላይ ምክክር

በየመን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትናንት ብራስልስ ውስጥ የመከሩት የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች ሰላም ማስፈን የሚቻለው በድርድር መኾኑን ገለጡ። የየመን ግጭት ለማስቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጀመረው የሰላም ጥረትንም እንደሚደግፉ አበክረው ተናግረዋል። በየመን የደረሰውን ቀውስ ለመታደግም ሚንሥትሮቹ ቁርጠኛ መኾናቸውን ዐስታውቀዋል።  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባወጣው ዘገባ መሠረት እስካሁን በየመን ግጭት የተነሳ ዐሥራ አምስት ሺህ ሰዎች ተገድለዋል። በጦርነቱ ምክንያት በተከሰተ ረሐብ ደግሞ 85,000 ህጻናት ሞተዋል። 
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ