1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለጦርነቱ ማብራሪያ ተጠየቀ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2014

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ  ፍትሕ (ኢዜንማ)ን የሚወክሉ 4 የምክር ቤት አባላት ለምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በፃፉት ደብዳቤ እንዳሉት መንግሥት ጦርነቱን ለማጠናቀቅ ያቀደበትን ጊዜ፣ ከሕዝብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠብቀዉን ድጋፍ ማወቅ ይፈልጋሉ።

https://p.dw.com/p/42D4f
EZEMA Partei Äthiopien Addis Abeba
ምስል Yohannes G/Egziabher/DW

የኢዜማ እንደራሴዎች ስለጦርነቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዲያብራሩ ጠቀቁ

 

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለሚደረገዉ ጦርነት ለሐገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ እንዲሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ እንደራሴዎች ጠየቁ።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ  ፍትሕ (ኢዜንማ)ን የሚወክሉ 4 የምክር ቤት አባላት ለምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በፃፉት ደብዳቤ እንዳሉት መንግሥት ጦርነቱን ለማጠናቀቅ ያቀደበትን ጊዜ፣ ከሕዝብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠብቀዉን ድጋፍ ማወቅ ይፈልጋሉ።ተወካዮቹ እንደሚሉት አሁን የሚደረገዉ ጦርነት እና በሐገሪቱ ላይ «የተደቀነ» ያሉትን አደጋ ለመከላከል መንግሥት የሚያደርገዉን ጥረትና ዕቅዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዲያብራሩላቸዉ ይፈልጋሉ።ደብዳቤዉ ለምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ እንደደረሰ መልስ እንደሚሰጥ የአፈ ጉባኤዉ ረዳት አስታዉቀዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ