1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ዶ/ር አብይ ንግግር የተቃዋሚዎች አስተያየት

ሰኞ፣ መጋቢት 24 2010

ተቃዋሚዎች ዶክተር አብይ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ምንም አለማለታቸው እና  የነጻነት እጦት ፈጥሯቸዋል የሚባሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚከተሉትን የማሻሻያ መርህ ግልጽ አለማድረጋቸው ቅር አሰኝቷቸዋል።

https://p.dw.com/p/2vNec
Äthiopien Vereidigung Premierminister Abiy Ahmed
ምስል picture-alliance/AA/M. W. Hailu

የተቃዋሚዎች አስተያየት

ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ ያሰሙት ንግግር የሚደነቅ ቢሆንም ንግግራቸውን በተግባር መተርጎም መቻላቸው ግን አጠያያቂ ነው ሲሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች አስታወቁ። ከዚህ ሌላ መሪዎቹ ዶክተር አብይ ያነሳሉ ብለው ከጠበቋቸው ጉዳዮች መካከል ያላነሷቸው በመኖራቸውም ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ከመካከላቸው ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ምንም አለማለታቸው እና  የነጻነት እጦት ፈጥሯቸዋል የሚባሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚከተሉትን የማሻሻያ መርህ ግልጽ አለማድረጋቸው ይገኙበታል። የዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ