1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስማርት ፎን በአፍሪቃ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 11 2008

ስማርት ፎን በመባል የሚታወቀዉ የዘመናዊዉ ቴክኒዎሎጂ ዉጤት የሆነዉ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ ጥቅም ላይ ከዋለ ሁለት አስርት ዓመታት አልፈዉታል።

https://p.dw.com/p/1Jjna
Symbolbild Whatsapp-Dialog
ምስል picture-alliance/dpa/B. Pedersen

ስማርት ፎን

የዚህ ስልክ ሥራዉ በርቀት ከሚገኝ ወዳጅ ዘመድ በድምጽ ብቻ ማገናኘት ከመሆን አልፎ ከኢንተርኔት አገልግሎት ተገናኝቶ ሰዎች ብዙም ሳይንቀሳቀሱ ባሉበት የሚፈልጉትን መረጃ በእጃቸዉ እንዲያገኙት ማስቻሉ ጥቅሙን አጉልቶታል። የዛሬ ሃያ ዓመት እንዲህ ያለዉን ቴክኒዎሎጂ በእጅ መያዝ ብርቅ ነበር። ዛሬ ደግሞ ሰዎች በየጎዳናዉ በእጃቸዉ ጨብጠዉ ዓይናቸዉን ከእሱ ሳይነቅሉ ሲንቀሳቀሱ መመልከት ተለምዷል። ተንቀሳቃሹ ዘመናዊ የመገናኛ ቴክኒዎሎጂ ዉጤት የሆነዉ ስማርት ፎን፤ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቱም ለመረጃ ስርጭት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ እየታየ ነዉ። የመረጃ ቁጥብነት እና እጥረት በሚታይባቸዉ እንደ አፍሪቃ ባሉ አህጉሮች ደግሞ የሕዝቡ ዋነኛ የሃሳብ ማንሸራሸሪያ መንገድ ሆነዋል። የዕለቱ ሳይንስና ኅብረተሰብ 20 ዓመት ያሳለፈዉን ይህን ቴክኒዎሎጂ ይቃኛል።

ቴሬሳ ክሪኒንገር /ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ