1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስም ማለት ምን ማለት ነዉ

Azeb Tadesseእሑድ፣ ሐምሌ 12 2001

ስም ማለት ምን ማለት ነዉ? ብለዉ ያዉቃሉ። በአገራችን የስም አሰጣጥ ዘዴ በባህላዊዉም ሆነ በዘመናዊዉ የህብረተሰብ ክፍል ብዙ ገጽታዎች ያሉት ክስተት ነዉ።

https://p.dw.com/p/IsgP

በዚህም የተነሳ ብሄረሰቡ ወይም ማህበረሰቡ የሚሰይማቸዉ መጠሪያዎቹ የብሄረሰቡን እምነት የመግለጽ ልማድ ይታይባቸዋል። ለምሳሌ አቶ አማረ ልጃቸዉን ሁሉባንተ አማረ ሲሉት፣ በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን ደግሞ አቶ ይግዛዉ ወንድ ልጅ ቢወልዱ ሃይለስላሴ ይግዛዉ ብለዉታል አሉ። በአብዮቱም ዘመን የተወለዱ የዘመኑን ስም ይዘዉ ነበር። ልሳነ ብዙ በሆነችዉ በኢትዮጽያችን ለስም የምንጠቀምበት ቋንቋ ህብረተሰቡ ለየትኛዉ ቋንቋ ዝንባሌ እንዳለዉ ያሳየና። ስለ ስም አወጣጥ ባህል የሚያጫዉቱን ምሁር የዛሪዉ የባህል መድረክ እንግዳችን ናቸዉ ኢትዮጽያዊ ምሁር ጋብዘናል ያድምጡ።