1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስንዴና ተዛመተ የተባለው «ዋግ» ፣

ረቡዕ፣ ነሐሴ 30 2004

በግብርናው ዘርፍ ፣ የስንዴ ይዞታ ተማራማሪ ጠበብት በቤይጂንግ ፤ ቻይና ፣4ቀናት በመምከር ትናንት ስብሰባውን መደምደማቸው ተነግሯል። ከ 13 ዓመት በፊትለመጀመሪያ ጊዜ በምሥራቅ አፍሪቃ የተከሠተ የስንዴ ጸር (ዋግ ) ወደ የመንና ኢራን

https://p.dw.com/p/1645C
Deutschland Landwirtschaft Getreidefeld
ምስል picture-alliance/chromorange

የተዛመተ መሆኑ ሲታወቅ፤ እስከሩቅ ምሥራቅ እንዳይዛመት ሥጋት አለ። ከአርሶ አደሮችና ሳይንቲስቶች የተሰበሰበ መረጃ ይዞ የተነሣው «ረስት ትራከር» የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት፣ በ 27 አዳጊ አገሮች፤ የስንዴን ይዞታ በመመርመር ላይ መሆኑን ጠቁሞአል።

Flash-Galerie Themen der Grünen Landwirtschaft
ምስል Petra Reinartz/Fotolia

Borlaug Global Rust Initiative (BGRI) የተባለው ድርጅት ምክትል ሊቀ-መንበር  ሮኒ ኮፍማን፣ ከአዳጊ አገሮች፤ አፍጋኒስታን ፤ ባንግላዴሽ፤ ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ፣ ህንድ ፤ ኬንያ፣ ኔፖልና ፓኪስታን፤ ዋግን የሚቋቋሙ የተለያዩ የስንዴ አዝርእትን  በማልማት እንደሚታገሉ ቢጠቅሱም፤ በቅርቡ ፣ ይኸው ዋግ ይበልጥ የሚያሠጋት አገር ኢትዮጵያ  ናት  ማለታቸው አላስደነገጠንም ማለት አይቻልም።

Weizen mit Kühen, Landwirtschaft, Argrarpolitik
ምስል AP

በመሆኑም ፤ ከቅርብ ከሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን ጠበብት መካከል፤ በእንግሊዝኛው Ethio-Organic Seed Action የተሰኘው፣ በተለይ በግብርናው ቴክኒክ ዘርፍ ላይ የተሠማራው ፤ የመንግሥት ያልሆነው ድርጅት ዋና ኀላፊ የሆኑትን ባለሙያ፣  ዶ/ር ረጋሣ ፈይሣን ፣ አሁን የተነገረለት ስንዴን ፍሬቢስ የሚያደርገው ዋግ በአዲስ መልክ ያገረሸ ፣ ወይስ የቆየ ነው? የኢትዮጵያ የስንዴ አዝርእት ይዞታስ በምን ላይ ይገኛል በማለት ጠይቄአቸው ነበር።---

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ