1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስዊስ ህዝቧና ኢትዮጵያዊዉ አቶ ምስጢረ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 23 2005

በአሁኑ ጊዜ በስዊዘርላንድ የስደተኞች አቀባበል መርህ ከቀድሞው እየጠበቀ መምጣትና ፣ ሌሎችም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተፅእኖዎች በበስዊዘርላንድ የተገን ጠያቂዎችን ህይወት አስቸጋሪ አድርጎታል እንደ አቶ ምስጢረ ።

https://p.dw.com/p/19HPX
ምስል Reuters

አቶ ምስጢረ ኃይለ ሥላሴ ከዛሬ 35 ዓመት አንስቶ ስዊትዘርላንድ ነው የሚኖሩት ።
አቶ ምስጢረ ስዊዘርላንድ ከመሄዳቸው በፊት እስራኤል አሜሪካንም ነበሩ ። ከእነዚህ ሃገሮች ግን
በሰላማዊነቷ በመረጋጋቷ ስዊዘርላንድን መርጠዋታል ።
ስዊዘርላንድ አቶ ምስጢረ ጋዜጠኝነት አጥንተዋል በንግድ አስተዳደርም የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው ። አሁን በሂሳብ አያያዝ ሥራ ላይ ነው የተሰማሩት ። በትርፍ ጊዜያቸውም በጋዜጠኝነቱ ሞያ ይሰራሉ ። መፅሄት ያዘጋጁ ነበር ለመጽሄቶችና ለአንዳንድ ድረ ገፆችም ፅሁፎችን ይልካሉ ። «አድማስ» ህትመቱ ከተቋረጠ ብዙ አመታት ያስቆጠረ የአቶ ሚስጥረ መፅሄት ነው።
አድማስ መታተሙ ቢቆምም አቶ ምስጢረ መፃፍ አላቋረጡም ። እንደ በፊቱም ባይሆን Ethiosport.com ለተባለ ድረ ገፅ ፅሁፎቻቸውን ያበረክታሉ ።
በአሁኑ ጊዜ በስዊዘርላንድ የስደተኞች አቀባበል መርህ ከቀድሞው እየጠበቀ መምጣትና ፣ ሌሎችም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተፅእኖዎች በበስዊዘርላንድ የተገን ጠያቂዎችን ህይወት አስቸጋሪ አድርጎታል እንደ አቶ ምስጢረ ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ