1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞችን የሚያሰለጥነዉ ሪኮኔክት

ሐሙስ፣ ሰኔ 12 2006

የዓለም የስደተኞች ቀን በነገዉ ዕለት ይታሰባል። በያዝነዉ በተለይም ጦርነት እና ግጭት ከሚካሄድባቸዉ ሃገራትና አካባቢዎች የሚሰደዱት ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR ባለፈዉ ወር ነዉ የጠቆመዉ።

https://p.dw.com/p/1CMDj
Flüchtlingsboot vor der australischen Küste
ምስል Scott Fisher/Getty Images

ሰዎች ከሀገራቸዉ ተሰደዉ በሚጠጉባቸዉ ሃገራት ለደህንነታቸዉ ሊሰጣቸዉ ከሚገባቸዉ ከለላ ሌላ በሄዱበት የተሻለ ኑሮ እንዲያገኙ የሚረዱ ተቋማት አሉ። ብሪታንያ ዉስጥ የሚንቀሳቀስ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ስደተኞች ጥገኝነት ባገኙባት ሀገር ራሳቸዉን አሻሽለዉ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ አስችሏል። በጎርጎሪዮሳዊዉ 2003ዓ,ም የተቋቋመዉ ሪኮኔክት የተሰኘዉ ይህ ድርጅት እስካሁን 50 ስደተኞችን ደረጃዉን በጠበቀ ሁኔታ በመምህርነት አሠልጥኗል ከእነዚህ ዉስጥም 13ቱ ኢትዮጵያዉያን እንደሆኑ የሎንዶን ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

ድልነሳ ጌታነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ