ስደተኞች ከመስመጥ ዳኑ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2008ማስታወቂያ
የኢጣሊያ ባሕር ኃይል ሜድትራኒያን ባሕር ላይ ሲቀዝፉ ለአደጋ የተጋለጡ ከ6ሺሕ አምስት መቶ በላይ ስደተኞች ትናንት ማዳኑን አስታወቀ።የባሕር ሐይሉ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በአራት አነስተኛ ጀልባዎች ተሳፍረዉ ይጓዙ የነበሩት ስደተኞች ቁጥር ጀልባዎቹ ከሚሸከሙት በላይ ሥለነበር ጀልባዎቹ ለመስመጥ ተቃርበዉ ነበር።የስደተኞቹን ሕይወት በማዳኑ ጥረት ከባሕር ሐይሉ ባልደረቦች በተጨማሪ የበጎ ፍቃደኛ ነብስ አድን ሰራተኞችም ተሳትፈዉ ነበር።አንዲት የኖርዌ መርከብም ከሰባት መቶ በላይ ስደተኞች ከመስመጥ አድናለች።ሥለስደተኞቹ ጉዞና ከመስመጥ ሥለማዳኑ ጥረት የሮም ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።
ተኽለእግዚ ገብረየሱስን
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ