1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደትን ለመግታት ያለመዉ የአዉሮጳ ኮሚሽን

ሐሙስ፣ ጥር 18 2009

የአዉሮጳ ኮሚሽን በማዕከላዊዉ ሜዲትራኒያን አቋርጠዉ በደቡብ አዉሮጳ በኩል የሚገቡትን ተሰዳጆች ቁጥር ለመቀነስ የሚያስችሉ ተጨማሪ ርምጃዎችን ለመዉሰድ ማቀዱን አመለከተ። ኮሚሽኑ ዕቅዱን በቅርቡ ማልታ ላይ በሚካሄደዉ የመሪዎች ጉባኤ ለማፀደቅ መዘጋጀቱንም አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/2WSlR
Elendsflüchtlinge aus Afrika
ምስል picture-alliance/dpa/dpaweb

Beri. Brüssel (EC New measures on Migration 2017) - MP3-Stereo

 የአዉሮጳ ኅብረት ቀደም ሲል ስደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዳይገቡ ለመቆጣጠር እና ለመመለስ የሚያስችሊ ስምምነቶችን ከቱርክ እና ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር መፈራረሙ ይታወሳል። የአሁኑ ተጨማሪ ርምጃ በተለይ የቫሌታዉን ስምምነት ለማጠናከርና ይበልጥም ዉጤታማ ለማድረግ መሆኑን ትናንት በብራስልስ በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለቻ የሰጡት የኅብረቱ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ፌደሪካ ሞጎረኒ እና የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር ዲሚትሪስ አብራምፖሎስ ማስታወቃቸዉን በስፍራዉ የተገኘዉ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ የላከዉ ዘገባ ያመለክታል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ