1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስጋት ላይ የወደቀዉ የአፍሪቃ የኤኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር

ቅዳሜ፣ ኅዳር 13 2007

የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የጀርመን የቅርብ አጋር የሆነችዉን አፍሪቃዊት ሃገር ደቡብ አፍሪቃን ጎብኝተዋል።

https://p.dw.com/p/1DrZh

የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የጀርመን የቅርብ አጋር የሆነችዉን አፍሪቃዊት ሃገር ደቡብ አፍሪቃን ጎብኝተዋል። በደቡብ አፍሪቃ የጀርመኑ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የኤኮኖሚ አለመመረጋትና ደካማ ጎኖች አሉት በሚል ስጋት ላይ በመዉደቁ፤ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ላይ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎአል። ስጋት ላይ የወደቀዉ የአፍሪቃ የኤኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር በሚል የዶቼ ቬለዉ ክላዉስ ሽቴከር ከፕሪቶርያ በላከዉ ዘገባ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በደቡብ አፍሪቃዉ ጉብኝታቸዉ አንድ ምልክትን ማሳረፍ እንደሚፈልጉ በዘገባዉ አትቶአል።