1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስጋት የተደቀነበት የሰሜንና የደቡብ ሱዳን የሰላም ውል

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 16 2001

የሞተው ሰው ቁጥር ሁለት ሚልዮን ደርሶዋል፤ የተፈናቀሉት ደግሞ አራት ሚልዮን። ከአንድ ሚልዮን ተኩል የሚበልጡ ስደተኞች በውጭ ሀገሮች ይኖራሉ። የደቡብ ሱዳን ደቡባዊ ከፊል የሀያ ሁለት ዓመቱ የርስበርስ ጦርነት እጅግ ተጎድቶዋል።

https://p.dw.com/p/JG4a
በዋው ከተማ የተሰማራው የተመደ ሰላም አስከባሪ ጓድምስል DW


ይኸው ጦርነት ከአምስት ዓመት በፊት እአአ በ 2005 ዓም በሱዳን መንግስትና በደቡብ ሱዳን ህዝብ ነጻ አውጪ ጦር መካከል በናይቫሻ ኬንያ በደረሱት የሰላም ስምምነት ሊያበቃ መቻሉ ይታወሳል። በሰላሙ ስምምነት እንደሰፈረው፡ የደቡብ ሱዳን ህዝብ ውሉ ከተፈረመ ከስድስት ዓመታት በኋላ እአአ በ 2011 ዓም በሬፈረንደም ከሱዳን ጋር በመቆየቱ ወይም ነጻ መንግስት በመመስረቱ ጥያቄ መካከል መወሰን ይጠበቅበታል። ይሁንና፡፡ይኸው የህዝበ ውሳኔ ዕለት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር፡ ባካባቢው አዲስ ጦርነት እንዳይነሳ የሚታየው የህዝቡ ስጋት ከፍ እያለ ሄዶዋል።

ዳንየል ፔልስ/አርየም ተክሌ

MM