1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስጋት ያንዣበበት ደን፤ በጋምቤላ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2003

በጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ ጉማሪ ቀበሌ የሚገኝ በአገር በቀል ዛፎችና በብዝሃ ህይወት ስብጥር የበለፀገ የደን አካባቢ ለባለሃብት መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/RN3S
ምስል picture-alliance/dpa

የአካባቢዉ ኗሪዎች ጉዳዩን ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል በማሳወቅ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነዉ መሬት ለባለሃብት ተሰጥቶ እንዳይመነጠር ጠይቀዋል፤ ጉዳያቸዉ እስከአገሪቱ ፕሬዝደንት ድረስም ደርሶ በደብዳቤ የተነሳዉ ጥያቄ ትኩረት ተሰጥቶት፤ ለባለሃብቱ አማራጭ እንዲፈለግ የተጠየቀበት ሁኔታም አለ። ሰሞኑን የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸዉ ወገኖች ሁለት ሄክታር የሚሆን አካባቢ መመንጠሩን ቢጠቁሙም፤ የጋምቤላ ኢንቨስትመንት ቢሮ በበኩሉ እንዲህ ያለ አካባቢ ለባለሃብት አልተሰጠም ይላል። በዕለቱ ጤናና አካባቢ መሰናዶ ጉዳዩ ተስተናግዷል። የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋም ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማንቀሳቀሻ የተመደበዉ በርካታ ቢሊዮን ዶላር ጠንካራ ቁጥጥር እንዲደረግበት ተጠይቋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ