1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፓኝና የህብረቱ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 29 2002

ከጎርጎሮሳውያኑ 2010 ዓ.ም መጀመሪያ አንስቶ የአውሮፓ ህብረት የ52 ዓመታት ታሪክ ተቀይሯል ።

https://p.dw.com/p/LMhk
የስፔይን የአውሮፓ ህብረት የፕሬዝዳንትነት አርማ

በየስድስት ወሩ በዙር የሚደርሰውን ህብረቱን የመምራት ሀላፊነት የሚረከቡት አባል ሀገራት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሙሉ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን አይኖራቸውም ።አሁን ስራቸውን የሚያግዝ ቋሚ ባለስልጣን አግኝተዋል የሊዝበኑ ውል መተግበር ከጀመረ ከአንድ ወር በኃላ ስፓኝ የተረከበችው የአሁኑ የስድስት ወራት የመሪነት ስልጣንዋ ከቀድሞዎቹ ይለያል ።

Jose Luis Rodriguez Zapatero
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆሴ ማኑዌል ሮድሪጌዝ ዛፓቴሮምስል AP

ሁለቱ አዳዲስ የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሊዝበኑ ውል መሰረት በአውሮፓ ህብረት ፅህፈት ቤት ብራሰልስ የሚካሄዱ ዐብይ ጉባኤዎችን ሲመሩ የስፓኝ ሚና ከሁለቱ ባለሥልጣናት ያነሰ ነው የሚሆነው ። አንዱ ተግባሯ የህብረቱን ከፍተኛ ሀላፊዎች ማገዝ ነው ። በሚኒስትሮች ደረጃ የሚካሄዱ ዋና ዋና ስብሰባዎችንና ከህብረቱ ውጭ ከሆኑ አገራት ጋር የሚካሄዱ ጉባኤዎችንም ማስተናገድ ይጠበቅባታል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ