1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ አኅጉራዊውን የቻን ውድድር ለማዘጋጀት አልጠየኩም አለች

ሰኞ፣ መስከረም 22 2010

በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደውን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ማመልከቻ ማስገባቷን ካፍ አስታወቀ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲ ባሻ ግን "ለካፍ ደብዳቤ አልፃፍንም" ሲሉ አስተባብለዋል።

https://p.dw.com/p/2l7gZ
Werbeball für den Afrika-Cup 2010
ምስል picture-alliance/dpa/B. Fonseca

የመስከረም 22 ቀን 2010 ዓ.ም የስፖርት መሰናዶ

 የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በድረ-ገፁ ከኬንያ የተነጠቀውን ውድድር ለማዘጋጀት ማመልከቻቸውን አቅርበዋል ካላቸው አገራት መካከል ኤኳቶሪያል ጊኒ እና ሞሮኮ ይገኙበታል። የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ባካሔደው ጉባኤ የውድድሩን አዘጋጅ አገር በ15 ቀናት ውስጥ አሳውቃለሁ ብሎ ነበር። ውድድሩን ልታዘጋጅ ተመርጣ የነበረችው ኬንያ አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎችን ባለማሟላቷ እድሉን ተነጥቃለች። የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው እና ቻን በሚል መጠሪያው የሚታወቀው ውድድር 16 ሐገራት ይሳተፋሉ። ሐገራቱ የሚመርጧቸው ተጨዋቾች ግን በአገራቸው ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱ ብቻ ናቸው። በዛሬው የስፖርት መሰናዶ ይኸንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ዜናዎች ተካተውበታል። 
ሐይማኖት ጥሩነሕ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ