1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ነሐሴ 1 2009

አትሌት ሞ ፋራህ በድል ዩዜይን ቦልት በሽንፈት ከአትሌቲክስ በጡረታ መሰናበታቸው እና የኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና የ10 ሺህ ሜትር ድንቅ አጨራረስ የዘንድሮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና አስገራሚ ክስተቶች ተብለዋል።

https://p.dw.com/p/2hq30
UK Leichtathletik WM London 2017 | 10.000 Meter Frauen | Siegerehrung
ምስል DW/H. Tiruneh

ስፖርት

ለንደን ብሪታንያ በመካሄድ ላይ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያ እስከዛሬ በአንድ የወርቅ እና በሁለት የብር ሜዳልያ በሜዳልያው ሰንጠረዥ ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥላ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች። አትሌት ሞ ፋራህ በድል ዩዜይን ቦልት በሽንፈት ከአትሌቲክስ በጡረታ መሰናበታቸው እና የኢትዮጵያዊቷ  አትሌት አልማዝ አያና የ10 ሺህ ሜትር ድንቅ አጨራረስ የዘንድሮው የዓለም አትሌቲክስ  ሻምፕዮና አስገራሚ ክስተቶች ተብለዋል። የዓለም አትሌቲክ ሻምፕዮና ዝርዝር ዘገባ ፣የዓለማችን ውድ ክፍያ የተፈጸመበት የብራዚላዊው እውቅ የእግር ኳስ ተጫዋች የኔይማር ከባርሴሎና የእግር ኳስ ክለብ ወደ ፓሪ ሳን ዠርማ ዝውውር፣የአውሮጳ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ እና ሌሎችም ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አበይት ስፖርታዊ ክንውኖች በስፖርት ዝግጅታችን ተካተዋል።

 

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ