1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 8 2009

ከ203 ሃገራት የተዉጣጡ 2200 አትሌቶች የተካፈሉበት የዘንድሮዉ የለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በወንዶች አምስት ሺህ ሲጠበቅ የነበረዉን የእንግሊዙን ሯጭ ትዉልደ ሶማሊያ ሞ ፋራህን ህልም በለወጠ ድል የወርቅ ባለቤት ሆናለች። በሴቶች ደግሞ ብሯን አጥልቃለች።

https://p.dw.com/p/2iD5S
IAAF London Leichtathletik WM- Muktar Kedir Und Mo Farah
ምስል DW/H. Tiruneh

ስፖርት፣ ነሀሴ ስምንት፣ 2009 ዓም

የለንደኑ የዘንድሮዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተለያዩ ግድፈቶች ቢታዩበትም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር  ያለዉ ተመልካች የተገኘበት እና ብዙ ትኬት የተሸጠበት በመሆን ግን ታሪክ አስመዝግቧል።  የዕለቱ የስፖርት ጥንቅር ትናንት የተጠናቀቀዉ የለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና  አጠቃላይ ሂደት የቃኘ ቃለ መጠይቅ፤ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሑራዊ ቡድን፤ እንዲሁም ሌሎች  የስፖርት እንቅስቃዎች ላይ ያተኮሩ አጫጭር ዘገባዎችንም አካቷል። ቅንብሩን የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ