1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ግንቦት 21 2009

በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዮ ሀገሮች የተደረጉት የጎዳና እና የ መሮጫ ሚዳ አትሌቲክስ ውድድሮች ማራኪና አዝናኝ ነበሩ ።አሚሪካ ዩጄን  በተደረጋው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የ አራት ጊዜ የወርቅ ሚዳልያ ባለቢት ሞ ፋራህ የአመቱን ፈጣን ሰአት በማስመዝገብ ሲያሸንፍ ለውድድሩ ልብ አንጠልጣይ መሆን ምክንያቱ የ 19 አመቱ ሽንጠ ረጅሙ ዮሚፍ ቀጀልቻ ነው

https://p.dw.com/p/2dmbO
Formel 1 Monaco Grand Prix 2017 | Kimi Raikkonen vor Sebastian Vettel
ምስል Reuters/M. Rossi

ስፖርት፣ ግንቦት 21፣ 2009 ዓም

 29 ተወዳዳሪዋች የተሰለፉበት የወንዶች 5000 ሚትር ውድድር የ 34አመቱ የ 4 ግዜ የኦሎምፒክ አሽናፊ ሞ ፋራህ 13,00,70 ሰከንድ በመግባት ፈጣን ሰአት ሲጨርስ አትሌት በሪዮ ኦሎንፒክ ባናየውም ከአመት በፊት በዙሁ አሚሪካ  በተደረገው በ3000 ሚትር የቢት ውስጥ ውድድር አኣሸናፊ የ19 አመቱ ወጣት  ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ ጝሩም ፍክክር አድርጎ 13 ደቂቃ 01 ሰከንድ ከ 21 በመግባት በርቀቱ ተስፋ የሚጣልበት አትሌት መሆኑን አሳይትዋል ።ኬንያዊው አትሌት በሶስተኛነት ጨርሷል።

አርብ ዳይመንድ ሊግን ለማስዋብ በተደረገ የሲቶች 5000 ሚትር ርቀት 16 የርቀቱ ባለሙያ አትሊቶች የተካፈሉብትን ውድድር በመጨረሻ ብቻወን የነገሰችበት ገንዘቤ ዲባባ ነበረች የአለም 1500 ሻምፕዮን  አና ክብረወስን ባለቤት ያለ ምንም ችግር አሽንፋለች ።ገንዘቤ ያሰበችውን የርቀቱን ፈጣን ሰአት ባታስመዘግብም  ማሸ ነፍ ብቻ ሰይሆን እንዲህ ይሮጣል ስትል ጥንካሪዋ ን ያሰየችበት  ይህ ውድድር  ከ 10 ሳምንት በኋላ  በለንዶን የ ሚደረገው የአለም ሻምፕዮና በናፍቆት አንዲጠበቅ ምክንያት ሆናለች ።

በ ካናዳ ትላንት በተካሂድ የሩጫ ውድድር ከ 1 እስከ ሶስት ኤትዮጵያውያን ሴት አትሊቶች አሽንፈዋል የ 25 አመቷ ጉትኒ ኤማና 2:30:18 አንደኛ ህይወት ገብረኪዳንን–2:30:53 ሁለተኛ አበራሽ ፈይሳ 2:31:27 ሶስተኛ ሆናለች ።

ሃና ደምሴ 

ኂሩት መለሰ