1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ጥር 5 2006

የእስፖርት አንዱ ዓላማ ፣ በዓለም ህዝብ መካከል መግባባትና ፤ ማለፊያ ግንኙነት እንዲፈጠር ማብቃት ነው፤ ስለሆነም፤ ይህን ዐቢይ ቁም ነገር ልብ ያለው የቀድሞው የ«ቺካጎ ቡልስ» ኮከብ የቅርጫት ኳስ ተጫዋችና የሰሜን ኮሪያው ወጣት አምባገነን መሪ ኪም

https://p.dw.com/p/1Apwu
ምስል DW/H. Turuneh

ዮንግ ዑን ወዳጅ መሆኑ የሚነገርለት ዴኒስ ሮድማን፣ በሰሜን ኮሪያው መሪ የልደት በዓል ፤ ከሌሎች ኮከብ ተጫዋቾች ጋር «የበጎ ፈቃድ ውድድር »ያሉትን ጨዋታ ማሳየታቸው ታውቋል።

Äthiopien Kenenisa Bekele
ምስል picture-alliance/dpa

ለምን ወደ ሰሜን ኮሪያ ሄደ? ለምን ስለ ለሰብአዊ መብት አልጠየቀም በማለት ለነቀፉት የአገሩ ሰዎች፤ የተሻለ ውጤት የሚገኘው ለዘብ ባለ አቀራረብ መሆኑን ሳይጠቁም አላለፈም። ቤይጂንግ አኤሮፕላን ጣቢያ እንደደረሰ የሰሜን ኮሪያ ህዝብን በዚያ የሚፈጸመው ያሳዝነኛል፤ እኔ በበኩሌ ጥሩ ነገር ብቻ ነው ለማድረግ የሞከርሁ፣ ግን «እኔ ፕሬዚዳንትም ፤ አምባሳደርም አይደለሁም -- እኔ ዴኒስ ሮድማን ነኝ » ነው ያለው ባጭሩ። ወደ ሳምንታዊው የአስፖርት ዘገባ እናምራ--

የጀርመን የአንደኛ ምድብ እግር ኳስ ክለቦች ፣ ከታኅሳስ 14 ቀን አንስቶ እስከ ጥር 15 ፣ በክረምት ዕረፍት ሳቢያ ውድድር ስለሌላቸው ፤ አንዳንዶቹ ወደ ሞቃት አገሮች በመጓዝ ልምምድ ሲያደርጉ መሰንበታቸው ታውቋል። በብሪታንያ ፤ እስፓኝ ፤ ኢጣልያና በመሳሰሉት ሃገራት ግን በዛሬው የእስፖርት ዝግጅት እንደምንገነዘበው ውድድሩ እንደቀጠለ ነው።

Symbolbild Sport Homosexualität
ምስል imago/Sven Simon

እግር ኳስ ፤ አትሌቲክስ ፣ እስፖርትና ግብረ ሶዶማዊነት ፣ እንዲሁም የሜዳ ቴኒስ ፣ በዛሬው የእስፖርት ክፍለ ጊዜ ትኩረት የሚደረግባቸው ናቸው ።ለጥንቅሩ ሃይማኖት ጥሩነህ---

ሃይማኖት ጥሩነህ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ