1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ነሐሴ 17 2002

የበርሊኑ አትሌቲክስ ውድድር እና ሌላው የሳምንቱ የስፖርት ክንውን

https://p.dw.com/p/Ou8C
ምስል dpa - Report

ጀርመን በበርሊን ባዘጋጀችው እና ትናንት በተካሄደው ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ የስቴድየም ውድድር በሶስት ሺህ እና በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር ሩጫ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ታሪኩ በቀለ እና መኮንን ገብረ መድህን አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል። ኬንያዊው ዴቪድ ሩዲሻም አስራ ሶስት ዓመት ሙሉ በቀድሞው የዴንማርክ አትሌት ዊልሰን ኪፕኬቴር ተይዞ የቆየውን የስምንት መቶ ሜትሩን ሩጫ ክብረ ወሰን ሰብሮዋል። በአንድ መቶ ፡ በሁለት መቶ እና በአራት መቶ ሜትር ሩጫም አሜሪካውያኑ፡ ጃማይካናውያኑ፡ ካናዳውያኑ እና እንግሊዛውያኑ ድል ተቀዳጅተዋል።

ይልማ ሀይለሚካኤ/ሀና ደምሴ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ