1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊላንድ እና ጸረ የባህር ላይ ውንብድና

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 1 2003

በሰሜናዊ ሶማልያ የምትገኘው ሶማሊላንድ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ በሱስ አስያዥ ዕጽ እና በወንጀል አንጻር በሚታገለው የተመድ መስሪያ ቤት ርዳታ በአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ዩሮ ወጪ በርዕሰ ከተማ ሀርጌሳ የተሰራ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ወህኒ ቤት ከፈተች።

https://p.dw.com/p/RGeK
ምስል DW/Richard Lough

የቀድሞ የሶማልያ ፕሬዚደንት ሲያድ ባሬ እአአ በ 1991 ዓም ከስልጣን በተወገዱ ጊዜ ነጻነትዋን ያወጀችው እና ከዚያን ጊዜ ወዲህ ባካባቢው መረጋጋት የሰፈነባት ስርዓተ ዴሞክራሲን የምትከተለው ሶማሊላንድ የባህር ላይ ውንብድናን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጎን በመሆን ለመታገል ቆርጣ መነሳትዋን አረጋግጣለች።

DW