1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊያና ሁል-አቀፍ የሰላም ንግግር ለማስፈን የተያዘ ጥረት

ዓርብ፣ ጥር 15 2001

መቀመጫውን አሥመራ ላይ ያደረገው "ሕብረት ለሶማሊያ ዳግም ነጻነት" በአሕጽሮት ARS የተሰኘ እንቅስቃሴ ማንኛውም የውጭ ሃይል አገሪቱን ለቆ እስካልወጣ ድረስ ሰላምን ለማስፈን እንደማይቻልና በትግሉ እንደሚቀጥልም እስከቅርቡ በያጋጣሚው ሲያስገነዝብ መቆየቱ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/Gf8J
ምስል AP

ቡድኑ አሁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ከሞቃዲሾ ከወጣ በኋላ ሁል-አቀፍ የሶማሊያ የሰላም ንግግር ለመጀመር ጥረት እያደረገ መሆኑን የሕብረቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ዶር/ሣላህ-ሞሐመድ-አሊ አሥመራ ላይ ገልጸዋል። ሣላህ አያይዘው እንዳስረዱት በወቅቱ ሶሥት ሰዎችን ያቀፈ የሕብረቱ ልዑካን ቡድን ወደ ሞቃዲሾ ተጉዞ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖችን ለማግባባት እየጣረ ነው። ከአሥመራ ጎይቶም ቢሆን! ◄