1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊያና የጋዜጠኞች ስቃይ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 22 2003

ድንበር የለሹ ዓለም ዓቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት አር.ኤስ.ኤፍ ዛሬ በሚጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2010 በዓለም ዙሪያ የተገደሉት ጋዜጠኞች ቁጥር ከ2009 ጋር ሲነጻጸር በ25 በመቶ መቀነሱን ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/Qldz
ምስል picture alliance / dpa

በ2010 በ25 ሀገራት ከስራቸው ጋር በተያያዘ 57 ጋዜጠኞች መገደላቸውን ያመላከተው የአር.ኤስ. ኤፍ ሪፖርት ፓኪስታን በዓመቱ የጋዜጠኞች ግድያ የበረከተባት ሲል በመጀመሪያ ደረጃ አስቀምጧታል። ሶማሊያ ከ8ቱ ለጋዜጠኞች የከፉ ሀገራት አንዷ ሆና ተጠቅሳለች። መሰረቱን መቅዲሾ ያደረገው ሸበሌ ራዲዮ ሰራተኞቹን በግድያና በስደት እያጣ እንደሆነ ገልጿል። መሳይ መኮንን የሸበሌ ሬዲዮ አዘጋጅን በማነጋገር ያሰናዳው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ