1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊያዉያን ስደተኞች እና ዳዳብ

ሰኞ፣ ጥር 16 2008

ኬንያ ዉስጥ በትልቁ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ዳዳብ ከሚገኙት አብዛኞቹ ስደተኞች የሶማሊያ ዜጎች ናቸዉ። በተለይም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2011ዓ,ም በርካቶች ድርቅ እና ረሀብ ሽሽት ከሶማሊያ ተሰደዉ የገቡት በዚሁ መጠለያ ጣቢያ እንደሆነ ይነገራል።

https://p.dw.com/p/1Hjbi
Dürre in Ostafrika 2011
ምስል picture-alliance/abaca

[No title]

ካለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ጀምሮ የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR በዳዳብ መጠለያ ጣቢያ ከሚገኙ «ፈቃደኛ» የሆኑትን ወደሶማሊያ መመለስ መጀመሩን አስታዉቋል። ድርጅቱ እንደሚለዉ ባለፈዉ ዓመት 6,000 ሶማሊያዉያን ስደተኞችን መልሷል፤ ዘንድሮ ደግሞ 50ሺ ለመመለስ አቅዷል። ሶማሊያዉያኑ ወደሀገራቸዉ መመለሱን ባይጠሉትም በቂ መጠለያ አለማግኘት እና የትምህርት ቤቶች አለመኖር፤ ከፀጥታዉ ስጋት ጋር ተዳምሮ ችግር ፈጥሮባቸዋል። ለአንዳንዶቹ ደግሞ በመጠለያ ጣቢያዉ ያለዉ የፀጥታ ሁኔታ ሀገራቸዉን እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል። ስለሁኔታዉ ናይሮቢ የሚገኘዉን ጋዜጠኛ አነጋግረነዋል።

ፋሲል ግርማ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ