1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶሪያ የድርድር ተስፋ

ረቡዕ፣ ጥር 18 2008

በድርድሩ ላይ የሚካፈሉት አማፂያን ማንነት እና ደረጃቸዉ አሁንም እያወዛገበ ነዉ። በተለይ የሶሪያ ኩርዶች በድርድሩ መካፈል-አለመካፈላቸዉ ሩሲያን ከዩናይትድ ስቴትስ፤ ሳዑዲ አረቢያን ከቱርክ እያወዛገበ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Hkm8
ሶሪያ የድርድር ተስፋ
ምስል Reuters/D. Balibouse

[No title]

የሶሪያ መንግሥትና መንግሥትን የሚወጉ አማፂ ሐይላት ተወካዮች በመጪዉ አርብ ዤኔቭ-ስዊዘርላንድ ዉስጥ የሠላም ድርድር ሊጀምሩ ነዉ። በድርድሩ ላይ የሚካፈሉት አማፂያን ማንነት እና ደረጃቸዉ አሁንም እያወዛገበ ነዉ። በተለይ የሶሪያ ኩርዶች በድርድሩ መካፈል-አለመካፈላቸዉ ሩሲያን ከዩናይትድ ስቴትስ፤ ሳዑዲ አረቢያን ከቱርክ እያወዛገበ ነዉ። ያም ሆኖ በሶሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ስቴፋን ደ ሚስቱራ እንዳሉት አብዛኞቹ አማፂያን በድርድሩ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝርዝር አጠናቅሮታል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ